Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 9:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ከሳ​ኦ​ልም ቤት አንድ ብላ​ቴና ነበረ፤ ስሙም ሲባ ነበረ፤ ወደ ዳዊ​ትም ጠሩት፤ ንጉ​ሡም፥ “አንተ ሲባ ነህን?” አለው። እር​ሱም፥ “እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ነኝ” አለ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 በዚያ ጊዜ ከሳኦል ቤት ሲባ የሚባል አንድ አገልጋይ ስለ ነበር፣ ወደ ዳዊት እንዲሄድ ነገሩት። ንጉሡም፣ “ሲባ የምትባለው አንተ ነህን?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፣ “አዎን እኔ አገልጋይህ ነኝ” አለ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በዚያን ጊዜ ከሳኦል ቤት ጺባ የሚባል አንድ አገልጋይ ስለ ነበር ወደ ዳዊት ጠሩት። ንጉሡም፥ “ጺባ የምትባለው አንተ ነህን?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፥ “አዎን እኔ አገልጋይህ ነኝ” አለ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ከሳኦል ቤተሰብ ጺባ የሚባል አንድ አገልጋይ ነበረ፤ እርሱም ወደ ዳዊት እንዲሄድ ተነገረው፤ ዳዊትም “አንተ ጺባ ነህን?” ሲል ጠየቀው። ጺባም “ጌታ ሆይ! እነሆ አገልጋይህ ነኝ!” ሲል መለሰ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ከሳኦልም ቤት ሲባ የሚባል አንድ ባሪያ ነበረ፥ ወደ ዳዊትም ጠሩት፥ ንጉሡም፦ አንተ ሲባ ነህን? አለው። እርሱም፦ እኔ ባሪያህ ነኝ አለ።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 9:2
7 Cross References  

ከእ​ር​ሱም ጋራ ከብ​ን​ያም ወገን የሆኑ ሺህ ሰዎች ነበሩ፤ የሳ​ኦ​ልም ቤት አገ​ል​ጋይ ሲባ ከእ​ር​ሱም ጋር ዐሥራ አም​ስቱ ልጆ​ቹና ሃያው አገ​ል​ጋ​ዮቹ ነበሩ፤ በን​ጉ​ሡም ፊት በቀ​ጥታ ወደ ዮር​ዳ​ኖስ ሄዱ።


ያለ​ው​ንም ሁሉ ለዮ​ሴፍ በእጁ አስ​ረ​ከ​በው፤ ከሚ​በ​ላ​ውም እን​ጀራ በቀር ምንም የሚ​ያ​ው​ቀው አል​ነ​በ​ረም። ዮሴ​ፍም መልኩ ያማረ፥ ፊቱም እጅግ የተ​ዋበ ነበር።


አብ​ር​ሃ​ምም ሎሌ​ውን፥ የቤ​ቱን ሽማ​ግሌ፥ የከ​ብ​ቱን ሁሉ አዛዥ አለው፦


ንጉ​ሡ​ንም የማ​ሻ​ገር ሥራ ሠሩ። የን​ጉ​ሡ​ንም ቤተ ሰብእ ያነሡ ዘንድ፥ በፊ​ቱም የቀና ሥራን ይሠሩ ዘንድ ወደ ማዶ ተሻ​ገሩ። ንጉ​ሡም ዮር​ዳ​ኖ​ስን ከተ​ሻ​ገረ በኋላ የጌራ ልጅ ሳሚ በን​ጉሡ ፊት፦ በግ​ን​ባሩ ወደቀ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements