Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 8:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ዳዊ​ትም ከእ​ርሱ ሺህ ሰረ​ገ​ላ​ዎ​ችን፥ ሰባት ሺህ ፈረ​ሰ​ኞ​ችን፥ ሃያ ሺህም እግ​ረ​ኞ​ችን ያዘ፤ ዳዊ​ትም የሰ​ረ​ገ​ለ​ኛ​ውን ፈረስ ሁሉ ቋንጃ ቈረጠ፤ ለራ​ሱም መቶ ሰረ​ገ​ላ​ዎ​ችን ብቻ አስ​ቀረ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ዳዊትም አንድ ሺሕ ሠረገሎች፣ ሰባት ሺሕ ፈረሰኞችና ሃያ ሺሕ እግረኞች ማረከበት። ቍጥራቸው መቶ የሆነ የሠረገላ ፈረሶች ብቻ ሲቀሩ ሌሎቹን በሙሉ ቋንጃቸውን ቈረጠ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ዳዊትም አንድ ሺህ ሠረገሎች፥ ሰባት ሺህ ፈረሰኞችና ሃያ ሺህ እግረኞች ማረከበት። ቁጥራቸው መቶ የሆነ የሠረገላ ፈረሶች ብቻ ሲቀሩ ሌሎቹን በሙሉ ቋንጃቸውን ቆረጠ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ዳዊትም ከሀዳድዔዜር አንድ ሺህ ሰባት መቶ ፈረሰኞችንና ኻያ ሺህ እግረኛ ወታደሮችን ማረከበት፤ ሠረገላ ለመሳብ የሚያገለግሉ አንድ መቶ ፈረሶችን አስቀርቶ፥ የቀሩትን ፈረሶች በሙሉ ቋንጃቸውን ቈርጦ ከአገልግሎት ውጪ እንዲሆኑ አደረገ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ዳዊትም ከእርሱ ሺህ ሰባት መቶ ፈረሰኞች፥ ሀያ ሺህም እግረኞች ያዘ፥ ዳዊትም የሰረገለኛውን ፈረስ ሁሉ ቋንጃ ቈረጠ፥ ለመቶ ሰረገላ ብቻ አስቀረ።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 8:4
8 Cross References  

ኢያ​ሱም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረ​ገ​ባ​ቸው፤ የፈ​ረ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ቋንጃ ቈረጠ፤ ሰረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ፊት ይሞቱ ዘንድ ነገ በዚህ ጊዜ ሁሉን በእ​ጅህ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና አት​ፍ​ራ​ቸው፤ የፈ​ረ​ሶ​ቻ​ቸ​ውን ቋንጃ ትቈ​ር​ጣ​ለህ፤ ሰረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ለህ” አለው።


ንጉሥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተማ​ም​ኖ​አ​ልና፥ በል​ዑ​ልም ምሕ​ረት አይ​ና​ወ​ጥም።


ዳዊ​ትም ከእ​ርሱ አንድ ሺህ ሰረ​ገ​ሎች፥ ሰባት ሺህም ፈረ​ሰ​ኞች፥ ሃያ ሺህም እግ​ረ​ኞች ወሰደ፤ ዳዊ​ትም ለመቶ ሰረ​ገ​ሎች የሚ​ሆ​ኑ​ትን ብቻ አስ​ቀ​ርቶ የሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹን ፈረ​ሶች ቋንጃ ቈረጠ።


ሰሎ​ሞ​ንም ለሰ​ረ​ገ​ሎቹ ዐራት ሺህ እን​ስት ፈረ​ሶች ነበ​ሩት፤ ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረ​ሰ​ኞ​ችም ነበ​ሩት፤ በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችም ከተ​ሞች ከን​ጉሡ ጋር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አኖ​ራ​ቸው። ሰሎ​ሞ​ንም ከወ​ንዙ ጀምሮ እስከ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ምድ​ርና እስከ ግብፅ ድን​በር ድረስ በነ​ገ​ሥ​ታቱ ሁሉ ላይ ንጉሥ ነበር።


ለእ​ርሱ ፈረ​ሶ​ችን እን​ዳ​ያ​በዛ፥ ሕዝ​ቡ​ንም ወደ ግብፅ እን​ዳ​ይ​መ​ልስ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ በዚ​ያች መን​ገድ መመ​ለ​ስን አት​ድ​ገም ብሎ​አ​ልና።


በም​ክ​ራ​ቸው ሰው​ነቴ አት​ገ​ና​ኛ​ቸው፤ ዐሳ​ቤም በአ​መ​ፃ​ቸው አት​ተ​ባ​በ​ርም፤ በቍ​ጣ​ቸው ሰውን ገድ​ለ​ዋ​ልና፤ በገዛ ፈቃ​ዳ​ቸ​ውም የሀ​ገ​ርን ሥር ቈር​ጠ​ዋ​ልና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements