Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 8:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ዳዊ​ትም ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንን መታ፤ በም​ድ​ርም ጥሎ በገ​መድ ሰፈ​ራ​ቸው፤ በሁ​ለ​ትም ገመድ ለሞት፥ በአ​ን​ድም ገመድ ለሕ​ይ​ወት ሰፈ​ራ​ቸው፤ ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንም ለዳ​ዊት ገባ​ሮች ሆኑ፤ ግብ​ርም አመ​ጡ​ለት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እንዲሁም ዳዊት ሞዓባውያንን ድል አደረጋቸው፤ በመሬት ላይ አጋድሞ በገመድ ለካቸው፤ በገመድ ከተለኩትም ሁለት እጅ ሲገድል፣ አንድ እጅ ግን በሕይወት ይተው ነበር። ስለዚህ ሞዓባውያን የዳዊት ተገዦች ሆኑ፤ ገበሩለትም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እንዲሁም ዳዊት ሞዓባውያንን ድል አደረገ፤ በመሬት ላይ አጋድሞ በገመድ ለካቸው፤ በገመድ ከተለኩትም ሁለት እጅ ሲገድል፥ አንድ እጅ ግን በሕይወት ይተው ነበር። ስለዚህ ሞዓባውያን የዳዊት ተገዢዎች ሆኑ፤ ገበሩለትም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ቀጥሎም ንጉሥ ዳዊት ሞአባውያንን ድል አደረገ፤ እስረኞቹ በመሬት ላይ እንዲጋደሙ አድርጎ ከየሦስቱ ሰዎች ሁለት ሁለቱ በሞት እንዲቀጡ አደረገ። ስለዚህም ሞአባውያን የእርሱ ተገዢዎች በመሆን ይገብሩለት ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ሞዓብን መታ፥ ሞዓባውያንንም በምድር ጥሎ በገመድ ሰፈራቸው፥ በሁለትም ገመድ ለሞት፥ በአንድም ገመድ ሙሉ ለሕይወት ሰፈራቸው፥ ሞዓባውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፥ ግብርም አመጡለት።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 8:2
22 Cross References  

አየ​ዋ​ለሁ፥ አሁን ግን አይ​ደ​ለም፤ እባ​ር​ከ​ዋ​ለሁ፥ በቅ​ርብ ግን አይ​ደ​ለም፤ ከያ​ዕ​ቆብ ኮከብ ይወ​ጣል፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰው ይነ​ሣል፥ የሞ​ዓ​ብ​ንም አለ​ቆች ይመ​ታል፤ የሤ​ት​ንም ልጆች ሁሉ ይማ​ር​ካል።


እን​ዲሁ ለስ​ምህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እዘ​ም​ራ​ለሁ ምኞ​ቴን ሁል​ጊዜ ትሰ​ጠኝ ዘንድ።


ዳዊ​ትም በደ​ማ​ስቆ ሶርያ ጭፍ​ሮች አኖረ፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ለዳ​ዊት ገባ​ሮች ሆኑ፤ ግብ​ርም አመ​ጡ​ለት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዳዊ​ትን በሄ​ደ​በት ሁሉ ጠበ​ቀው።


ክፉ​ዎች ሰዎች ግን፥ “ያድ​ነን ዘንድ ይህ ሰው ማን ነው?” ብለው ናቁት፤ እጅ መን​ሻም አላ​መ​ጡ​ለ​ትም።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስ​ንም አት​ስሙ፤ የአ​ሦር ንጉሥ እን​ዲህ ይላል፦ በሕ​ይ​ወት ልት​ኖሩ ብት​ወ​ድዱ ሁላ​ችሁ ወደ እኔ ውጡ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ሁም ከወ​ይ​ና​ች​ሁና ከበ​ለ​ሳ​ችሁ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ከጕ​ድ​ጓ​ዳ​ች​ሁም ውኃ ትጠ​ጣ​ላ​ችሁ፤


ልጆ​ቹም ድሃ አደ​ጎች ይሁኑ፥ ሚስ​ቱም መበ​ለት ትሁን።


አሞ​ና​ው​ያ​ንም ለዖ​ዝ​ያን ገበሩ፤ እጅ​ግም በር​ትቶ ነበ​ርና ዝናው እስከ ግብፅ መግ​ቢያ ድረስ ተሰማ።


ሞዓ​ብ​ንም መታ፤ ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንም ለዳ​ዊት ገባ​ሮች ሆኑ፤ ግብ​ርም አመ​ጡ​ለት።


የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ስል​ም​ና​ሶር በእ​ርሱ ላይ ዘመተ፤ ሆሴ​ዕም ተገ​ዛ​ለት፤ ግብ​ርም አመ​ጣ​ለት።


አክ​ዓ​ብም ከሞተ በኋላ ሞዓብ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ዐመፀ።


በው​ስ​ጥ​ዋም የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ አው​ጥቶ በመ​ጋ​ዝና በብ​ረት መቈ​ፈ​ሪያ በብ​ረት መጥ​ረ​ቢ​ያም ሥር አኖ​ራ​ቸው፤ በሸ​ክላ ጡብ እቶ​ንም አሳ​ለ​ፋ​ቸው። በአ​ሞን ልጆች ከተ​ሞች ሁሉ እን​ዲሁ አደ​ረገ። ዳዊ​ትም፥ ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ።


ሳኦ​ልም መን​ግ​ሥ​ቱን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አጸና፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ካሉት ከጠ​ላ​ቶቹ ሁሉ ጋር፥ ከሞ​ዓ​ብም፥ ከአ​ሞ​ንም ልጆች፥ ከኤ​ዶ​ም​ያ​ስም፥ ከቢ​ዖ​ርም፥ ከሱ​ባም ነገ​ሥ​ታት፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሁሉ ጋር ይዋጋ ነበር፤ በየ​ሄ​ደ​በ​ትም ሁሉ ድል ይነሣ ነበር።


በል​ቅሶ ሸለቆ ውስጥ በወ​ሰ​ን​ኻ​ቸው ስፍራ የሕግ መም​ህር በረ​ከ​ትን ይሰ​ጣ​ልና።


ዳዊ​ትም ከዚያ በሞ​ዓብ ምድር ወዳ​ለ​ችው ወደ መሴፋ ሄደ፤ የሞ​ዓ​ብ​ንም ንጉሥ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ደ​ር​ግ​ል​ኝን እስ​ካ​ውቅ ድረስ አባ​ቴና እናቴ ከአ​ንተ ጋር ይቀ​መጡ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለው።


የሞ​ዓ​ብ​ንም ንጉሥ ማለ​ደው፤ ዳዊ​ትም በአ​ንባ ውስጥ በነ​በ​ረ​በት ወራት ሁሉ በእ​ርሱ ዘንድ ተቀ​መጡ።


ሰሎ​ሞ​ንም ከወ​ንዙ ጀምሮ እስከ ግብፅ ምድር ዳርቻ እስከ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሀገር ድረስ በመ​ን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ላይ ነግሦ ነበር፤ ግብ​ርም ያመ​ጡ​ለት ነበር፤ በዕ​ድ​ሜ​ውም ሙሉ ለሰ​ሎ​ሞን ይገዙ ነበር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements