Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 8:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ታይም የአ​ድ​ር​አ​ዛር ጠላት ነበ​ርና ዳዊት አድ​ር​አ​ዛ​ርን ስለ ተዋ​ጋ​ውና ስለ ገደ​ለው፥ ታይ ልጁን ኢያ​ዱ​ራን ደኅ​ን​ነ​ቱን ይጠ​ይቅ ዘንድ፥ ይመ​ር​ቀ​ውም ዘንድ ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው፤ እር​ሱም የብ​ርና የወ​ርቅ የና​ስም ዕቃ ይዞ መጣ፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ቶዑ ከአድርአዛር ጋራ ሁልጊዜ ይዋጋ ስለ ነበር፣ ሰላምታና በአድርአዛር ላይ ስለ ተቀዳጀውም ድል የደስታ መግለጫ እንዲያቀርብለት፣ ልጁን ዮራምን ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው፤ እርሱም የብር፣ የወርቅና የናስ ዕቃ ይዞ መጣ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ቶዒ ከሀዳድዔዜር ጋር ሁልጊዜ ይዋጋ ስለ ነበር፥ ልጁን ዮራምን ወደ ንጉሥ ዳዊት ለሰላምታና በሀዳድዔዜር ላይ ሰለተቀዳጀውም ድል ደስታውን እንዲያቀርብለት ላከው፤ ልጁም የብር፥ የወርቅና የናስ ዕቃ ይዞ መጣ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ስለዚህም ንጉሥ ሀዳድዔዜርን ድል በመንሣቱ ሰላምታና የደስታ መግለጫ ያቀርብለት ዘንድ ልጁን ዮራምን ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው፤ ቀደም ሲልም ቶዒ በሀዳድዔዜር ላይ ጦርነት ሲያካሄድ የነበረ ነው፤ ዮራምም ከወርቅ፥ ከብርና ከነሐስ የተሠሩ ልዩ ልዩ ስጦታዎችን ለዳዊት ይዞለት ሄደ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ቶዑም ከአድርአዛር ጋር ሁልጊዜ ይዋጋ ነበርና ዳዊት አድርአዛርን ድል ስለ መታ ቶዑ ልጁን አዶራምን ደኅንነቱን ይጠይቅ ዘንድ፥ ይመርቀውም ዘንድ ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው፥ እርሱም የብርና የወርቅ የናስም ዕቃ ይዞ መጣ።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 8:10
9 Cross References  

እር​ሱም እስ​ራ​ኤ​ልን ከኀ​ጢ​አቱ ሁሉ ያድ​ነ​ዋል።


ቶዑም ከአ​ድ​ር​አ​ዛር ጋር ሁል​ጊዜ ይዋጋ ነበ​ርና ዳዊት አድ​ር​አ​ዛ​ርን ወግቶ ስለ መታው ደኅ​ን​ነ​ቱን ይጠ​ይ​ቀ​ውና ይመ​ር​ቀው ዘንድ ልጁን አዶ​ራ​ምን ወደ ዳዊት ላከው፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የወ​ር​ቅና የብር፥ የና​ስም ዕቃ ነበረ።


የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት ማሳ​ረግ በፈ​ጸመ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሳሙ​ኤል መጣ፤ ሳኦ​ልም እን​ዲ​ባ​ር​ከው ሊገ​ና​ኘው ወጣ።


በዚ​ያም ወራት የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ የባ​ል​ዳን ልጅ መሮ​ዳክ ባል​ዳን ሕዝ​ቅ​ያስ ታምሞ እንደ ተፈ​ወሰ ሰምቶ ነበ​ርና ደብ​ዳ​ቤና እጅ መን​ሻን፥ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ች​ንም ላከ​ለት።


የን​ጉ​ሡም አገ​ል​ጋ​ዮች ገብ​ተው፦ ‘እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ሎ​ሞ​ንን ስም ከስ​ምህ ይልቅ መል​ካም ያድ​ርግ፤ ዙፋ​ኑ​ንም ከዙ​ፋ​ንህ የበ​ለጠ ያድ​ርግ’ ብለው ጌታ​ቸ​ውን ንጉሡ ዳዊ​ትን መረቁ፤” ንጉ​ሡም በአ​ል​ጋው ላይ ሆኖ ሰገደ።


እር​ሱም ደኅ​ን​ነ​ታ​ቸ​ውን ጠየ​ቃ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “የነ​ገ​ራ​ች​ሁኝ ሽማ​ግሌ አባ​ታ​ችሁ ደኅና ነውን? ገና በሕ​ይ​ወት አለን?”


የሓ​ማ​ትም ንጉሥ ታይ ዳዊት የአ​ድ​ር​አ​ዛ​ርን ጭፍራ ሁሉ እንደ መታ ሰማ።


እር​ሱ​ንም ንጉሥ ዳዊት ከሀ​ገ​ሮች ሁሉ አም​ጥቶ ከቀ​ደ​ሰው ከወ​ር​ቁና ከብሩ ጋር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀደሰ፤


ብዙ​ዎ​ቹም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ ይዘው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ይመጡ ነበር፤ ለይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ለሕ​ዝ​ቅ​ያስ እጅ መንሻ ይሰጡ ነበር፤ እር​ሱም ከዚህ ነገር በኋላ በሕ​ዝብ ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አለ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements