Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 7:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 አቤቱ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሰ​ራ​ዊት ጌታ ሆይ፥ የባ​ሪ​ያ​ህን ጆሮ ከፈ​ትህ። አንተ፦ እኔ ቤት እሠ​ራ​ል​ሃ​ለሁ አልህ፤ ስለ​ዚ​ህም ባሪ​ያህ ይህ​ችን ጸሎት ወደ አንተ ይጸ​ልይ ዘንድ በልቡ አሰበ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 “አቤቱ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ‘እኔ ለአንተ ቤት እሠራልሃለሁ’ ብለህ ይህን ለባሪያህ ገልጸህለታል። ስለዚህ ባሪያህ ይህችን ጸሎት ወደ አንተ ለማቅረብ በልቡ ደፈረ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 አቤቱ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ሆይ፤ ‘እኔ ለአንተ ቤት እሠራልሃለሁ’ ብለህ ይህን ለአገልጋይህ ገልጸህለታል። ስለዚህ አገልጋይህ ይህችን ጸሎት ወደ አንተ ለማቅረብ ድፍረት አግኝቶአል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ ለአገልጋይህ ቤት እሠራለሁ ብለህ ስለ ገለጥክለት አገልጋይህ ይህን ጸሎት ወደ አንተ ለማቅረብ ድፍረት አግኝቶአል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 አቤቱ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ አንተ፦ እኔ ቤት እሠራልሃለሁ ብለህ ለባሪያህ ገልጠሃልና ስለዚህ ባሪያህ ይህችን ጸሎት ወደ አንተ ይጸልይ ዘንድ በልቡ ደፈረ።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 7:27
10 Cross References  

እኔም በዚህ በተቀመጡት በሕዝቤ ሽማግሌዎች ፊት እንድትገዛው አስታውቅህ ዘንድ አሰብሁ። መቤዠት ብትወድድ ተቤዥው፣ መቤዥት ባትወድድ ግን ከአንተ በቀር ሌላ ወራሽ የለምና፥ እኔም ከእንተ በኋላ ነኝና እንዳውቀው ንገረኝ አለው። እርሱም፦ እቤዥዋለሁ አለው።


ከን​ቱን የሚ​ና​ገር ይግ​ባና ይይ፤ ልቡ በላዩ ላይ ኀጢ​አ​ትን ሰበ​ሰበ፤ ወደ ሜዳ ይወ​ጣል ይና​ገ​ራ​ልም፥ በእ​ኔም ላይ ይተ​ባ​በ​ራል።


ገናም ሳኦል ሳይ​መጣ ከአ​ንድ ቀን በፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሳ​ሙ​ኤል ጆሮ​ውን ከፈ​ተ​ለት፥


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ አዋ​ላ​ጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ​ፈሩ ቤቶ​ችን አደ​ረ​ገ​ላ​ቸው።


የታ​መነ ካህን ለእኔ አስ​ነ​ሣ​ለሁ፤ በል​ቤም፥ በነ​ፍ​ሴም እን​ዳለ እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋል፤ እኔም የታ​መነ ቤት እሠ​ራ​ለ​ታ​ለሁ፤ ዘመ​ኑን ሁሉ እኔ በቀ​ባ​ሁት ሰው ፊት ይሄ​ዳል።


በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ፈራ​ጆ​ችን በሾ​ምሁ ጊዜ ከጠ​ላ​ቶ​ችህ ሁሉ አሳ​ር​ፍ​ሃ​ለሁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ፦ ቤት እን​ደ​ም​ት​ሠ​ራ​ለት ይነ​ግ​ር​ሃል፤ እሠ​ራ​ለ​ታ​ለሁ ብለ​ሃ​ልና።


እርሱ ለስሜ ቤት ይሠ​ራል፤ ዙፋ​ኑን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጸ​ና​ለሁ።


ባሪ​ያ​ዬም ዳዊት እን​ዳ​ደ​ረገ፥ ያዘ​ዝ​ሁ​ህን ሁሉ ብት​ሰማ፥ በመ​ን​ገ​ዴም ብት​ሄድ፥ በፊ​ቴም የቀ​ና​ውን ብታ​ደ​ርግ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንና ሥር​ዐ​ቴን ብት​ጠ​ብቅ፥ ከአ​ንተ ጋር እኖ​ራ​ለሁ፤ ለዳ​ዊ​ትም እንደ ሠራ​ሁ​ለት የታ​መነ ቤትን እሠ​ራ​ል​ሃ​ለሁ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ለአ​ንተ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements