Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 7:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 አቤቱ ሁሉን የም​ት​ገዛ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ አሁ​ንም ለባ​ሪ​ያ​ህና ለቤቱ የተ​ና​ገ​ር​ኸ​ውን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አጽ​ናው፤ አሁ​ንም እንደ ተና​ገ​ርህ አድ​ርግ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 “አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ ለባሪያህና ለቤቱ የሰጠኸውን ተስፋ ለዘላለም የጸና ይሁን፤ እንደተናገርኸውም ፈጽም፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 አሁንም ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ለአገልጋይህና ለቤቱ የሰጠኸውን ተስፋ ለዘለዓለም ጠብቅለት፤ እንደተናገርኸውም ፈጽም፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25-26 “አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ስለ እኔና ስለ ዘሮቼ የተናገርከውን የተስፋ ቃል ሁሉ ለዘለዓለም ፈጽም፤ ስምህ ለዘለዓለም ታላቅ ይሆን ዘንድ የተናገርከውን ፈጽም፤ ሰዎችም ልዑል እግዚአብሔር የእስራኤል አምላክ ነው ይላሉ። የባሪያህም የዳዊት ቤት በፊትህ የጸና ይሆናል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 አቤቱ አምላክ ሆይ፥ አሁንም ለባሪያህና ለቤቱ የተናገርኸውን ለዘላለም አጽናው፥ እንደ ተናገርህም አድርግ።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 7:25
11 Cross References  

“ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ስለ​ዚህ ደግሞ አደ​ር​ግ​ላ​ቸው ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ይሹ​ኛል፤ ሰው​ንም እንደ መንጋ አበ​ዛ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።


አን​ተም፦ ‘በር​ግጥ መል​ካም አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለሁ፥ ዘር​ህ​ንም ከብ​ዛቱ የተ​ነሣ እን​ደ​ማ​ይ​ቈ​ጠር እንደ ባሕር አሸዋ አደ​ር​ጋ​ለሁ ብለህ ነበር።’ ”


ሕዝ​ብ​ህ​ንም እስ​ራ​ኤ​ልን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕዝብ አድ​ር​ገህ አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ኸ​ዋል፤ አን​ተም፥ አቤቱ፥ አም​ላክ ሆነ​ሃ​ቸ​ዋል።


ስምህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ታላቅ ይሁን።


ይኸ​ውም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እኔ፦ ‘ልጆ​ችህ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን ቢጠ​ብቁ፥ በፊ​ቴም በፍ​ጹም ልባ​ቸ​ውና በፍ​ጹም ነፍ​ሳ​ቸው በእ​ው​ነት ቢሄዱ ከእ​ስ​ራ​ኤል ዙፋን ሰው አይ​ጠ​ፋም’ ብሎ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ያጸና ዘንድ ነው።


አሁ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ! ለባ​ሪ​ያህ ለአ​ባቴ ለዳ​ዊት የተ​ና​ገ​ር​ኸው ቃል እባ​ክህ እው​ነት ይሁን።


ባል​ዋም ሕል​ቃና፥ “በዐ​ይ​ንሽ ደስ ያሰ​ኘ​ሽን አድ​ርጊ፤ ጡትም እስ​ኪ​ተው ድረስ ተቀ​መጪ፤ ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ፍሽ የወ​ጣ​ውን ያጽና” አላት። ሴቲ​ቱም ልጅ​ዋን እያ​ጠ​ባች ጡት እስ​ኪ​ተው ድረስ ተቀ​መ​ጠች።


አሁ​ንም፥ አቤቱ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ ለባ​ሪ​ያህ ለዳ​ዊት የተ​ና​ገ​ር​ኸው ቃል ይጽና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements