Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 7:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ጌታዬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ አንተ ባሪ​ያ​ህን ታው​ቃ​ለ​ህና ዳዊ​ትስ ይና​ገ​ርህ ዘንድ የሚ​ጨ​ም​ረው ምን​ድን ነው?

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 “ዳዊት ከዚህ በላይ ምን ሊልህ ይችላል? ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ባሪያህን አንተ ታውቀዋለህ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ዳዊት ከዚህ በላይ ምን ሊልህ ይችላል? ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አገልጋይህን አንተ ታውቀዋለህና!

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እንግዲህ ምን ልልህ እችላለሁ? እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! እኔን ባሪያህን ታውቀኛለህ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ ባሪያህን ታውቃለህና ዳዊትስ ይናገርህ ዘንድ የሚጨምረው ምንድን ነው?

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 7:20
9 Cross References  

ሦስ​ተኛ ጊዜም፥ “የዮና ልጅ ስም​ዖን ሆይ፥ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ ጴጥ​ሮ​ስም ሦስት ጊዜ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን? ስላ​ለው ተከዘ፤ “ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታው​ቃ​ለህ፤ እኔም እን​ደ​ም​ወ​ድህ አንተ ታው​ቃ​ለህ” አለው፤ “እን​ኪ​ያስ ግል​ገ​ሎ​ችን ጠብቅ” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ፊቱን፥ የቁ​መ​ቱ​ንም ዘለ​ግታ አትይ፤ ሰው እን​ደ​ሚ​ያይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አያ​ይ​ምና ናቅ​ሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ልብን ያያል” አለው።


“አቤቱ፥ ከክፉ ሰው አድ​ነኝ፥ ከዐ​መ​ፀኛ ሰውም ታደ​ገኝ፥


ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ ኵላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።


እኛን በሚ​ቈ​ጣ​ጠር በእ​ርሱ በዐ​ይ​ኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተ​ራ​ቈ​ተና የተ​ገ​ለጠ ነው እንጂ በእ​ርሱ ፊት የተ​ሰ​ወረ ፍጥ​ረት የለም።


የሰ​ው​ንም ግብ​ሩን ሊነ​ግ​ሩት አይ​ሻም፤ እርሱ በሰው ያለ​ውን ያውቅ ነበ​ርና።


ጽድ​ቅ​ንና ፍር​ድን በማ​ድ​ረግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ይጠ​ብቁ ዘንድ፥ ልጆ​ቹ​ንና ቤቱን ያዝ​ዛ​ቸው ዘንድ እን​ዳ​ለው አው​ቃ​ለ​ሁና፤ ይህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ር​ሃም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ሁሉ ያደ​ር​ግ​ላ​ቸው ዘንድ ነው።”


እር​ሱም፥ “እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሠራ​ዊት አለቃ ነኝ፤ አሁ​ንም ወደ አንተ መጥ​ቼ​አ​ለሁ” አለ። ኢያ​ሱም ወደ ምድር በግ​ም​ባሩ ተደ​ፍቶ ሰገ​ደና፥ “በባ​ሪ​ያህ ዘንድ ምን አቁ​ሞ​ሃል?” አለው።


አንተ ባሪ​ያ​ህን ታው​ቀ​ዋ​ለ​ህና ለባ​ሪ​ያህ ስለ ተደ​ረ​ገው ክብር ዳዊት ጨምሮ የሚ​ለው ምን​ድን ነው?


Follow us:

Advertisements


Advertisements