Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 5:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ዳዊት በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ሆኖ እንደ ተቀባ ሰሙ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሁሉ ዳዊ​ትን ሊፈ​ልጉ ወጡ፤ ዳዊ​ትም በሰማ ጊዜ ወደ ምሽጉ ወረደ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ዳዊት በእስራኤል ሁሉ ላይ ንጉሥ ሆኖ መቀባቱን ፍልስጥኤማውያን በሰሙ ጊዜ፣ እርሱን ፍለጋ በሙሉ ኀይላቸው ወጡ፤ ዳዊትም ይህን ሰምቶ ወደ ምሽጉ ወረደ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ዳዊት በእስራኤል ላይ ንጉሥ ሆኖ መቀባቱን ፍልስጥኤማውያን በሰሙ ጊዜ፥ ፍልስጤማውያን ሁሉ ዳዊትን ለመፈለግ በሙሉ ኀይላቸው ወጡ፤ ዳዊት ግን ይህን ሰምቶ ወደ ምሽጉ ወረደ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ዳዊት በእስራኤል ላይ መንገሡን ፍልስጥኤማውያን ሰሙ፤ ስለዚህም ሠራዊታቸው ዳዊትን ለመማረክ ገሥግሦ ሄደ፤ ዳዊት የእነርሱን መምጣት በሰማ ጊዜ ወደ ተመሸገ ስፍራ ወረደ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ፍልስጥኤማውያንም ዳዊት በእስራኤል ላይ ንጉሥ ሆኖ እንደ ተቀባ ሰሙ፥ ፍልስጥኤማውያንም ሁሉ ዳዊትን ሊፈልጉ ወጡ፥ ዳዊትም በሰማ ጊዜ ወደ ምሽጉ ወረደ።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 5:17
11 Cross References  

በዚያ ጊዜም ዳዊት በም​ሽጉ ውስጥ ነበረ፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጭፍራ በዚያ ጊዜ በቤተ ልሔም ነበረ።


በዚ​ያም ጊዜ ዳዊት በም​ሽጉ ውስጥ ነበረ፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጭፍራ በቤተ ልሔም ነበረ።


እነ​ርሱ በእ​ም​ነት ተጋ​ደሉ፤ ነገ​ሥ​ታ​ትን ድል ነሡ፤ ጽድ​ቅን አደ​ረጉ፤ ተስ​ፋ​ቸ​ውን አገኙ፤ የአ​ና​ብ​ስ​ት​ንም አፍ ዘጉ ።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጭፍ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ ወደ አፌቅ ሰበ​ሰቡ፤ እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያ​ንም በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ባለው ውኃ ምንጭ አጠ​ገብ ሰፈሩ።


ኤሊ​ሳማ፥ ኤሊ​ዳሂ፥ ኤሊ​ፋ​ላት፥ ሶሜኤ፥ ኢያ​ሴ​ቦት፥ ናታን፥ ጋላ​ማ​ሄን፥ የበ​አር፥ ትሄ​ሱስ፥ ኤል​ፋ​ላት፥ ናጌድ፥ ናሬት፥ ያናታ፥ ሊሳ​ሚስ፥ በአ​ሊ​ማት፥ ኤል​ፋ​ላድ።


ይኸ​ውም ከሶ​ርያ ከሞ​ዓ​ብና ከአ​ሞን ልጆች፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም፥ ከአ​ማ​ሌ​ቅም፥ ከረ​አ​ብም ልጅ ከሱባ ንጉሥ ከአ​ድ​ር​አ​ዛር ምርኮ ያመ​ጣው ነው።


በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንና በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም መካ​ከል ደግሞ ጦር​ነት ሆነ፤ ዳዊ​ትም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር አገ​ል​ጋ​ዮቹ ወረዱ፤ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጋር ተዋጉ፤ ዳዊ​ትም ደከመ።


ከዚ​ህም በኋላ ዳዊት ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን መታ፤ አዋ​ረ​ዳ​ቸ​ውም፤ ዳዊ​ትም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ምር​ኮን ወሰደ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements