Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 4:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ዳዊ​ትም ጐል​ማ​ሶ​ቹን አዘዘ፤ ገደ​ሉ​አ​ቸ​ውም፤ እጆ​ቻ​ቸ​ው​ንና እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ቈር​ጠው በኬ​ብ​ሮን በውኃ መቆ​ሚያ አጠ​ገብ አን​ጠ​ለ​ጠ​ሉ​አ​ቸው። የኢ​ያ​ቡ​ስ​ቴን ራስ ግን ወስ​ደው በአ​በ​ኔር መቃ​ብር በኬ​ብ​ሮን ቀበ​ሩት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ስለዚህም ዳዊት የራሱን ሰዎች አዘዘ፤ እነርሱንም ገደሏቸው፤ እጅና እግራቸውንም ቈርጠው በኬብሮን ካለው ኵሬ አጠገብ ሰቀሏቸው። ነገር ግን የኢያቡስቴን ራስ ወስደው ኬብሮን በሚገኘው በአበኔር መቃብር አጠገብ ቀበሩት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ስለዚህም ዳዊት የራሱን ሰዎች አዘዘ፤ እነርሱንም ገደሏቸው፤ እጅና እግራቸውንም ቆርጠው በኬብሮን ካለው ኲሬ አጠገብ ሰቀሏቸው። ነገር ግን የኢያቡስቴን ራስ ወስደው ኬብሮን በሚገኘው በአበኔር መቃብር አጠገብ ቀበሩት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ወዲያውም ዳዊት እንዲገድሉአቸው ለወታደሮቹ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ ወታደሮቹም ሬካብንና በዓናን ገደሉአቸው፤ እጃቸውንና እግራቸውንም ቈርጠው በኬብሮን በሚገኘው ኲሬ አጠገብ እንጨት ላይ ሰቀሉአቸው፤ የኢያቡስቴንም ራስ ወስደው በዚያው በኬብሮን በሚገኘው በአበኔር መቃብር ውስጥ ቀበሩት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ዳዊትም ጕልማሶቹን አዘዘ፥ ገደሉአቸውም፥ እጃቸውንና እግራቸውን ቆርጠው በኬብሮን በውኃ መቆሚያ አጠገብ አንጠለጠሉአቸው። የኢያቡስቴንም ራስ ወስደው በአበኔር መቃብር በኬብሮን ቀበሩት።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 4:12
8 Cross References  

አበ​ኔ​ር​ንም በኬ​ብ​ሮን ቀበ​ሩት፤ ንጉ​ሡም ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ በመ​ቃ​ብሩ አጠ​ገብ አለ​ቀሰ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ለአ​በ​ኔር አለ​ቀ​ሱ​ለት።


ዳዊ​ትም ከብ​ላ​ቴ​ኖቹ አን​ዱን ጠርቶ፥ “ሂድና ግደ​ለው” አለው፤ ገደ​ለ​ውም።


በገ​ባ​ዖ​ንም ሰዎች እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት በተ​ራ​ራው ላይ ሰቀ​ሏ​ቸው። ሰባ​ቱም በአ​ን​ድ​ነት ወደቁ፤ እህል በሚ​ታ​ጨ​ድ​በ​ትም ወራት በገ​ብሱ መከር መጀ​መ​ሪያ ተገ​ደሉ።


የሳ​ኦ​ልም ጭፍራ አለቃ የኔር ልጅ አበ​ኔር የሳ​ኦ​ልን ልጅ ኢያ​ቡ​ስ​ቴን ወስዶ ከሰ​ፈር ወደ መሃ​ና​ይም አወ​ጣው፤


በፋ​ን​ታው ነግ​ሠ​ሃ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሳ​ኦ​ልን ቤት ደም ሁሉ መለ​ሰ​ብህ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ግ​ሥ​ት​ህን ለል​ጅህ ለአ​ቤ​ሴ​ሎም እጅ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​ታል፤ እነ​ሆም፥ አንተ የደም ሰው ነህና በመ​ከራ ተይ​ዘ​ሃል።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements