2 ሳሙኤል 24:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 ንጉሡም ከእርሱ ጋር የነበረውን የሠራዊት አለቃ ኢዮአብን፥ “የሕዝቡን ድምር አውቅ ዘንድ ከዳን ጀምሮ እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ሂድ፤ ሕዝቡንም ቍጠራቸው” አለው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 ስለዚህም ንጉሡ ኢዮአብንና ዐብረውት ያሉትን የጦር አዛዦች፣ “ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ወዳሉት የእስራኤል ነገዶች ሁሉ ሂዱ፤ ብዛታቸው ምን ያህል እንደ ሆነ ለማወቅ እንድችልም ተዋጊዎቹን መዝግቡ” አላቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 ስለዚህም ንጉሡ ኢዮአብንና አብረውት የነበሩትን የጦር አዛዦች፥ “ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ወዳሉት የእስራኤል ነገዶች ሁሉ ሂዱ፤ ምን ያኽል ሕዝብ እንዳለ ማወቅ ስለምፈልግ ሕዝቡን ቁጠሩ።” አላቸው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 ስለዚህም ዳዊት የጦሩ አዛዥ የሆነውን ኢዮአብን “የጦር መኰንኖችህን በማስከተል ከአገሪቱ ዳር እስከ ዳር ማለትም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ወዳሉት የእስራኤል ነገዶች ሁሉ ሄደህ ሕዝቡን ቊጠር፤ ምን ያኽል ሕዝብ እንዳለ ማወቅ እፈልጋለሁ” ሲል አዘዘው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 ንጉሡም ኢዮአብንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን የሠራዊት አለቆች፦ የሕዝቡን ድምር አውቅ ዘንድ ከዳን ጀምሮ እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ተመላለሱ፥ ሕዝቡንም ቍጠሩአቸው አላቸው። See the chapter |