2 ሳሙኤል 24:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ሕዝቡንም ከቈጠረ በኋላ ዳዊትን ልቡ መታው፤ ዳዊትም እግዚአብሔርን፥ “ባደረግሁት ነገር እጅግ በድያለሁ፤ አሁን ግን አቤቱ! ታላቅ ስንፍና አድርጌአለሁና የባሪያህን ኀጢአት ታርቅ ዘንድ እለምንሃለሁ” አለው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ዳዊት ተዋጊዎቹን ከቈጠረ በኋላ ኅሊናው ስለ ወቀሠው፣ “ባደረግሁት ነገር ታላቅ ኀጢአት ሠርቻለሁ፤ አሁንም እግዚአብሔር ሆይ፤ የአገልጋይህን በደል እንድታርቅ እለምንሃለሁ፤ የፈጸምሁት ታላቅ የስንፍና ሥራ ነውና” አለ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ዳዊት ሕዝቡን ከቆጠረ በኋላ ኅሊናው ወቀሰው፤ ዳዊትም ጌታን፥ “ባደረግሁት ነገር የፈጸምኩት ታላቅ ኃጢአት ነው፤ አሁን ግን፥ ጌታ ሆይ፤ የአገልጋይህን በደል ይቅር እንድትል እለምንሃለሁ፤ የፈጸምኩት ታላቅ የሞኝነት ሥራ ነውና” አለ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ነገር ግን ዳዊት ሕዝቡን ከቈጠረ በኋላ የኅሊና ወቀሳ ስላስጨነቀው እግዚአብሔርን “እኔ ይህን በማድረጌ ታላቅ በደል ፈጽሜአለሁ፤ የሞኝነት ሥራ ስለ ሠራሁም እባክህ ይቅር በለኝ!” ሲል ለመነ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ሕዝቡንም ከቈጠረ በኋላ ዳዊትን ልቡ መታው፥ ዳዊትም እግዚአብሔርን፦ ባደረግሁት ነገር እጅግ በድያለሁ፥ አሁን ግን፥ አቤቱ፥ ታላቅ ስንፍና አድርጌአለሁና የባሪያህን ኃጢአት ታርቅ ዘንድ እለምንሃለሁ አለው። See the chapter |