Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 22:49 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

49 ከጠ​ላ​ቶቼ የሚ​ያ​ወ​ጣኝ እርሱ ነው፤ በእ​ኔም ላይ ከቆሙ ከፍ ከፍ ታደ​ር​ገ​ኛ​ለህ፤ ከግ​ፈ​ኛም ሰው ታድ​ነ​ኛ​ለህ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

49 እርሱ ከጠላቶቼ እጅ ነጻ ያወጣኛል። አንተ ከጠላቶቼ በላይ ከፍ ከፍ አደረግኸኝ፤ ከጨካኝ ሰዎችም እጅ ታደግኸኝ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

49 ከጠላቶቼ እጅ ነጻ የሚያወጣኝ እርሱ ነው። በጠላቶቼ ላይ ከፍ ከፍ አደረግኸኝ፤ ከጨካኝ ሰዎችም እጅ ታደግኸኝ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

49 ከጠላቶቼም ታድነኛለህ። በጠላቶቼ ላይ ከፍ ከፍ ታደርገኛለህ፤ ከግፈኞችም ታድነኛለህ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

49 ከጠላቶቼ የሚያወጣኝ እርሱ ነው፥ በእኔም ላይ ከቆሙ ከፍ ከፍ ታደርገኛለህ፥ ከግፈኛ ሰው ታድነኛለህ።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 22:49
11 Cross References  

አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፤ ስማኝ፤ ወደ አንተ ስጮ​ኽም የል​መ​ና​ዬን ቃል አድ​ምጥ።


ልቤን ወደ ክፉ ነገር አት​መ​ል​ሰው፥ ዐመ​ፃን ከሚ​ያ​ደ​ርጉ ሰዎች ጋር ለኀ​ጢ​አት ምክ​ን​ያት እን​ዳ​ል​ሰጥ፤ ከም​ር​ጦ​ቻ​ቸ​ውም ጋር አል​ተ​ባ​በር።


ሰነፍ በልቡ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የለም ይላል። ረከሱ፥ በበ​ደ​ላ​ቸ​ውም ጐሰ​ቈሉ፤ በጎ ነገ​ርን የሚ​ያ​ደ​ር​ጋት የለም።


ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ አድ​ርጎ እን​ዳ​ዘ​ጋ​ጀው፥ ስለ ሕዝቡ ስለ እስ​ራ​ኤ​ልም መን​ግ​ሥ​ቱን ከፍ እን​ዳ​ደ​ረገ ዐወቀ።


ችግ​ረ​ኛ​ውን ከመ​ሬት ያነ​ሣ​ዋል፤ ምስ​ኪ​ኑ​ንም ከጕ​ድፍ ያነ​ሣ​ዋል፤ ከሕ​ዝቡ መኳ​ን​ንት ጋር ያስ​ቀ​ም​ጠው ዘንድ፥ የክ​ብ​ር​ንም ዙፋን ያወ​ር​ሰው ዘንድ።


ከዘሩ ሰው ይወ​ጣል፤ ብዙ ሕዝ​ብ​ንም ይገ​ዛል፥ መን​ግ​ሥ​ቱም ከአ​ጋግ ይልቅ ከፍ ከፍ ትላ​ለች፥ መን​ግ​ሥ​ቱም ትሰ​ፋ​ለች።


ኀያል ሆይ፥ ፍላ​ጻ​ዎ​ችህ የተ​ሳሉ ናቸው፥ አሕ​ዛብ በበ​ታ​ችህ ይወ​ድ​ቃሉ። በን​ጉሥ ጠላ​ቶች ልብ ውስጥ ይገ​ባሉ፥


እነ​ሆም፥ ኩሲ መጣ፤ ኩሲም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላ​ይህ የተ​ነ​ሡ​ትን ሁሉ ዛሬ እንደ ተበ​ቀ​ለ​ልህ ለጌ​ታዬ ለን​ጉሡ ወሬ አም​ጥ​ቻ​ለሁ” አለ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements