Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 22:48 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

48 በቀ​ሌን የሚ​መ​ል​ስ​ልኝ አም​ላክ ጽኑዕ ነው። አሕ​ዛ​ብን በበ​ታቼ ያስ​ገ​ዛ​ል​ኛል፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

48 በቀሌን የሚመልስልኝ፣ አሕዛብንም ከሥሬ የሚያስገዛልኝ እርሱ ነው፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

48 የሚበቀልልኝ አምላክ፥ ሕዝቦችን ከሥሬ የሚያስገዛልኝ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

48 እርሱ ጠላቶቼን ይበቀልልኛል፤ ሕዝቦችንም ከበታቼ አድርጎ ያስገዛልኛል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

48 በቀሌን የሚመልስልኝ አምላክ፥ አሕዛብን በበታቼ የሚያስገዛ፥

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 22:48
11 Cross References  

በየ​ቀኑ ሁሉ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፥ ለስ​ም​ህም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዓለም ምስ​ጋና አቀ​ር​ባ​ለሁ።


ኑ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይበ​ለን፤ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ንና ለመ​ድ​ኀ​ኒ​ታ​ች​ንም እልል እን​በል፥


ጠላ​ቶቹ ሁሉ ከእ​ግሩ በታች እስ​ኪ​ወ​ድቁ ድረስ ይነ​ግሥ ዘንድ አለ​ውና።


አቤቱ፥ በቅ​ኖች ሸንጎ በጉ​ባ​ኤም በፍ​ጹም ልቤ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።


እነ​ሆም፥ ኩሲ መጣ፤ ኩሲም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላ​ይህ የተ​ነ​ሡ​ትን ሁሉ ዛሬ እንደ ተበ​ቀ​ለ​ልህ ለጌ​ታዬ ለን​ጉሡ ወሬ አም​ጥ​ቻ​ለሁ” አለ።


የሳ​ዶቅ ልጅ አኪ​ማ​ሖስ ግን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጠ​ላ​ቶቹ እጅ እንደ ፈረ​ደ​ለት ፈጥኜ ሄጄ ለን​ጉሥ የም​ሥ​ራች ልን​ገ​ርን?” አለ።


ዳዊ​ትም ናባል እንደ ሞተ በሰማ ጊዜ፥ “ከና​ባል እጅ የስ​ድ​ቤን ፍርድ የፈ​ረ​ደ​ልኝ፥ ባሪ​ያ​ው​ንም ከክ​ፉ​ዎች እጅ የጠ​በቀ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የና​ባ​ልን ክፋት በራሱ ላይ መለሰ” አለ። ዳዊ​ትም ያገ​ባት ዘንድ አቤ​ግ​ያን እን​ዲ​ያ​ነ​ጋ​ግ​ሩ​ለት ላከ።


እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለጌ​ታዬ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቸር​ነት ሁሉ ያደ​ር​ግ​ል​ሃል፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ አለቃ አድ​ርጎ ይሾ​ም​ሃል፤


እነሆ፥ የል​ብ​ስህ ዘርፍ በእጄ እን​ዳለ ተመ​ል​ክ​ተህ ዕወቅ፤ የል​ብ​ስ​ህ​ንም ዘርፍ በቈ​ረ​ጥሁ ጊዜ አል​ገ​ደ​ል​ሁ​ህም፤ ስለ​ዚ​ህም በእጄ ክፋት፥ በደ​ልና ክዳት እን​ደ​ሌለ፥ አን​ተ​ንም እን​ዳ​ል​በ​ደ​ል​ሁህ ዕወቅ፤ አንተ ግን ነፍ​ሴን ልታ​ጠፋ ታጠ​ም​ዳ​ለህ።


የኢ​ያ​ቡ​ስ​ቴ​ንም ራስ ይዘው ወደ ዳዊት ወደ ኬብ​ሮን መጡ፤ ንጉ​ሡ​ንም፥ “ነፍ​ስ​ህን ይሻ የነ​በ​ረው የጠ​ላ​ትህ የሳ​ኦል ልጅ የኢ​ያ​ቡ​ስቴ ራስ እነሆ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዛሬ ከጠ​ላ​ትህ ከሳ​ኦ​ልና ከዘሩ ለጌ​ታ​ችን ለን​ጉሥ በቀ​ሉን መለ​ሰ​ለት” አሉት።


በፍ​ርድ ቀን እበ​ቀ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እግ​ራ​ቸው በሚ​ሰ​ና​ከ​ል​በት ጊዜ፥ የጥ​ፋ​ታ​ቸው ቀን ቀር​ቦ​አ​ልና፥ የተ​ዘ​ጋ​ጀ​ላ​ች​ሁም ፈጥኖ ይደ​ር​ስ​ባ​ች​ኋ​ልና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements