Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 21:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ንጉ​ሡም ለሳ​ኦል የወ​ለ​ደ​ቻ​ቸ​ውን የኢ​ዮ​ሄ​ልን ልጅ የሩ​ጻ​ፋን ሁለ​ቱን ልጆች ሄር​ሞ​ን​ስ​ቴ​ንና ሜም​ፌ​ቡ​ስ​ቴን፥ ለመ​ሓ​ላ​ታ​ዊ​ውም ለቤ​ር​ዜሊ ልጅ ለኤ​ስ​ድራ የወ​ለ​ደ​ቻ​ቸ​ውን የሳ​ኦ​ልን ልጅ የሜ​ሮ​ብን አም​ስ​ቱን ልጆች ወሰደ፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ነገር ግን ንጉሡ፣ የኢዮሄል ልጅ ሪጽፋ ለሳኦል የወለደቻቸውን ሁለቱን ወንዶች ልጆች ሄርሞንንና ሜምፊቦስቴን፤ የሳኦል ልጅ ሜሮብ ለመሓላታዊው ለቤርዜሊ ልጅ ለኤስድሪኤል የወለደችለትን ዐምስት ወንዶች ልጆች ጭምር ወሰደ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ነገር ግን ንጉሡ የአያ ልጅ ሪጽፋ ለሳኦል የወለደቻቸውን ሁለቱን ወንዶች ልጆች አርሞኒንና መፊቦሼትን፤ የሳኦል ልጅ ሜራብ ለመሖላታዊው ለባርዚላይ ልጅ ለአድሪኤል የወለደችለትን አምስት ወንዶች ልጆች ጭምር ወሰደ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ይሁን እንጂ ዳዊት የአያ ልጅ ሪጽፋ ለሳኦል የወለደቻቸውን ሁለቱን ወንዶች ልጆች አርሞኒንና መፊቦሼትን ወሰደ፤ እንዲሁም የሳኦል ልጅ ሜራብ የመሖላን ተወላጅ ለሆነው ለባርዚላይ ልጅ ለዐድሪኤል የወለደችለትን አምስት ወንዶች ልጆች ጨምሮ ወሰደ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ንጉሡም ለሳኦል የወለደቻቸውን የኢዮሄል ልጅ የሪጽፋን ሁለቱን ልጆች ሄርሞንንና ሜምፊቦስቴን ለመሓላታዊውም ለቤርዜሊ ልጅ ለኤስድሪኤል የወለደቻቸውን የሳኦልን ልጅ የሜሮብን አምስቱን ልጆች ወሰደ፥

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 21:8
4 Cross References  

ለሳ​ኦ​ልም የኢ​ዮ​ሄል ልጅ ሩጻፋ የተ​ባ​ለች ዕቅ​ብት ነበ​ረ​ችው፤ ኢያ​ቡ​ስ​ቴም አበ​ኔ​ርን፥ “ወደ አባቴ ዕቅ​ብት ለምን ገባህ?” አለው።


ነገር ግን የሳ​ኦል ልጅ ሜሮብ ዳዊ​ትን የም​ታ​ገ​ባ​በት ጊዜ ሲደ​ርስ ለሚ​ሆ​ላ​ዊው ለአ​ድ​ር​ኤል ተዳ​ረች።


የሳ​ኦ​ልም ወን​ዶች ልጆች ዮና​ታን፥ የሱዊ፥ ሚል​ኪሳ ነበሩ፤ የሁ​ለ​ቱም ሴቶች ልጆቹ ስም ይህ ነበረ፤ የታ​ላ​ቂቱ ስም ሜሮብ፥ የታ​ና​ሺ​ቱም ስም ሜል​ኮል ነበረ።


በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ የና​ሚ​ሶን ልጅ ኢዩን ቅባው፤ በፋ​ን​ታ​ህም ነቢይ ይሆን ዘንድ የአ​ቤ​ል​መ​ሁ​ላን ሰው የሣ​ፋ​ጥን ልጅ ኤል​ሳ​ዕን ቅባው፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements