Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 21:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ዳዊ​ትም የገ​ባ​ዖ​ንን ሰዎች፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ርስት ትባ​ርኩ ዘንድ ምን ላድ​ር​ግ​ላ​ችሁ? ማስ​ተ​ስ​ረ​ያ​ውስ ምን​ድን ነው?” አላ​ቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ዳዊትም ገባዖናውያንን፣ “ምን ላድርግላችሁ? የእግዚአብሔርን ርስት ትባርኩ ዘንድ ማስተስረያውን ምን ማድረግ አለብኝ?” ሲል ጠየቃቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ዳዊትም ገባዖናውያንን፥ “ምን ላድርግላችሁ? የጌታን ርስት ትባርኩ ዘንድ ማስተሰረያውን ምን ማድረግ አለብኝ?” ሲል ጠየቃቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ስለዚህም ዳዊት የገባዖንን ሰዎች በአንድነት ጠርቶ “የእግዚአብሔርን ሕዝብ ትመርቁ ዘንድ ቀድሞ በተፈጸመባችሁ ግፍ ፈንታ ካሣ የሚሆን አንድ ነገር ላደርግላችሁ እፈልጋለሁ፤ ታዲያ፥ ምን ላድርግላችሁ?” አላቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ዳዊትም የገባዖንን ሰዎች፦ የእግዚአብሔርን ርስት ትባርኩ ዘንድ ምን ላድርግላችሁ? ማስተሰረያውስ ምንድር ነው? አላቸው።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 21:3
9 Cross References  

በእ​ስ​ራ​ኤል ኀያ​ላን ዘንድ ሰላ​ምን ከሚ​ወ​ድ​ዱት አን​ድዋ ነኝ፤ አንተ ግን በእ​ስ​ራ​ኤል ያለ​ች​ውን ከተ​ማና እናት ከተ​ማን ለማ​ፍ​ረስ ትሻ​ለህ፤ ስለ​ም​ንስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ርስት ታጠ​ፋ​ለህ?”


ደግ​ሞም በቀ​ረ​በው ሁሉ እን​ዲህ ያደ​ርግ ነበር፥ በኦ​ሪት ሕግ ሁሉ በደም ይነጻ ነበር፤ ደም ሳይ​ረጭ ግን አይ​ሰ​ረ​ይም ነበር።


አሁ​ንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! የእ​ኔን የአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህን ቃል ስማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእኔ ላይ አስ​ነ​ሥ​ቶህ እን​ደ​ሆነ፥ ቍር​ባ​ን​ህን ይቀ​በል፤ የሰው ልጆች ግን ቢሆኑ፦ ሂድ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት አም​ልክ ብለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት ላይ እን​ዳ​ል​ቀ​መጥ ዛሬ ጥለ​ው​ኛ​ልና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ርጉ​ማን ይሁኑ።


ሰውስ ሰውን ቢበ​ድል ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ል​ዩ​ለ​ታል፤ ሰው ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቢበ​ድል ስለ እርሱ ወደ ማን ይጸ​ል​ዩ​ለ​ታል?” እነ​ርሱ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ጠ​ፋ​ቸው ወድ​ዶ​አ​ልና የአ​ባ​ታ​ቸ​ውን ቃል አል​ሰ​ሙም።


ተቀ​ባ​ይ​ነት ይኖ​ረው ዘንድ ስለ እር​ሱም ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለት ዘንድ እጁን በሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ራስ ላይ ይጭ​ናል።


በነ​ጋ​ውም ሙሴ ለሕ​ዝቡ፥ “እና​ንተ ታላቅ በደል ሠር​ታ​ች​ኋል፤ አሁ​ንም አስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ላ​ችሁ ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እወ​ጣ​ለሁ፤” አላ​ቸው።


ባሕሩ ይታ​ወክ ነበ​ርና፥ ታላቅ ማዕ​በ​ልም ተነ​ሥቶ ነበ​ርና፥ “ባሕሩ ጸጥ ይል​ልን ዘንድ እን​ግ​ዲህ ምን እና​ድ​ር​ግህ?” አሉት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements