Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 20:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በገ​ባ​ዖ​ንም ወዳ​ለው ወደ ታላቁ ድን​ጋይ በደ​ረሱ ጊዜ አሜ​ሳይ በፊ​ታ​ቸው መጣ፤ ኢዮ​አ​ብም የሰ​ልፍ ልብስ ለብሶ ነበር፤ በላ​ዩም መታ​ጠ​ቂያ ነበረ፤ በወ​ገ​ቡም ላይ ሰገባ ያለው ሰይፍ ታጥቆ ነበር፤ እር​ሱም ሲራ​መድ ሰይፉ ወደቀ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 በገባዖን ከታላቁ ቋጥኝ አጠገብ ሳሉ፣ አሜሳይ ሊገናኛቸው መጣ፤ ኢዮአብ የጦር ሜዳ ልብሱን ለብሶ ሰይፉን ከነሰገባው በወገቡ ላይ ታጥቆ ነበር፤ ወደ ፊት ራመድ እንዳለም ሰይፉ ከሰገባው ወጥቶ ወደቀ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በገባዖን ከታላቁ ቋጥኝ አጠገብ እንደ ደረሱ፥ አማሳይ ሊገናኛቸው መጣ፤ ኢዮአብ የጦር ሜዳ ልብሱን ለብሶ ሰይፉን ከሰገባው በወገቡ ላይ ታጥቆ ነበር፤ ወደ ፊት ራመድ እንዳለም ሰይፉ ከሰገባው ወጥቶ ወደቀ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 በገባዖን ወደሚገኘው ወደ ትልቁ ድንጋይ በደረሱ ጊዜ ዐማሣ አገኛቸው፤ በዚህን ጊዜ ኢዮአብ ሰይፉን በሰገባው ከቶ፥ ሰገባውንም በመታጠቂያው ላይ አስሮ ለጦርነት ተዘጋጅቶ ነበር፤ እየተራመደ ወደ ፊት ሲሄድ ሳለም ሰይፉ ወደቀ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በገባዖንም ወዳለው ወደ ታላቁ ድንጋይ በደረሱ ጊዜ አሜሳይ ሊገናኛቸው መጣ፥ ኢዮአብም የሰልፍ ልብስ ለብሶ ነበር፥ በላዩም መታጠቂያ ነበረ፥ በወገቡም ላይ ሰገባ ያለው ሰይፍ ታጥቆ ነበር፥ እርሱም ሲራመድ ሰይፉ ወደቀ።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 20:8
5 Cross References  

ኢዮ​አ​ብና ወን​ድሙ አቢ​ሳም በሰ​ልፍ በገ​ባ​ዖን ወን​ድ​ማ​ቸ​ውን አሣ​ሄ​ልን ገድሎ ነበ​ርና አበ​ኔ​ርን ይገ​ድ​ሉት ዘንድ ይጠ​ባ​በቁ ነበር።


የሶ​ር​ህያ ልጅ ኢዮ​አ​ብና የዳ​ዊት ብላ​ቴ​ኖች ከኬ​ብ​ሮን ወጥ​ተው በገ​ባ​ዖን ውኃ መቆ​ሚያ አጠ​ገብ ተገ​ና​ኙ​አ​ቸው፤ በው​ኃ​ውም መቆ​ሚያ በአ​ንዱ ወገን እነ​ዚህ፥ በሌ​ላ​ውም ወገን እነ​ዚያ ሆነው ተቀ​መጡ።


ራሱም ዮሐንስ የግመል ጠጉር ልብስ ነበረው፤ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የበረሓ ማር ነበረ።


ናዖ​ድም ሁለት አፍ ያላት ርዝ​መቷ አንድ ስን​ዝር የሆ​ነች ሰይፍ አበጀ፤ ከል​ብ​ሱም በታች በቀኝ በኩል በወ​ገቡ ታጠ​ቃት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements