| 2 ሳሙኤል 20:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 ነገሩ እንዲህ አይደለም፤ ከተራራማው ከኤፍሬም ሀገር የሚሆን የቢኮሪ ልጅ ሳቡሄ የሚባል አንድ ሰው ግን በንጉሡ በዳዊት ላይ እጁን አነሣ፤ እርሱን ብቻውን ስጡኝ፤ እኔም ከከተማዪቱ እርቃለሁ” አላት። ሴቲቱም ኢዮአብን፥ “እነሆ፥ ራሱ ከቅጥር ላይ ይጣልልሃል” አለችው።See the chapter አዲሱ መደበኛ ትርጒም21 ነገሩስ እንዲህ አይደለም፤ የኰረብታማው የኤፍሬሙ አገር ሰው፣ የቢክሪ ልጅ ሳቤዔ እጁን በንጉሡ በዳዊት ላይ አንሥቷል፤ እናንተ ይህን ሰው ብቻ ስጡኝ እንጂ እኔ ከተማዪቱን ትቼ እሄዳለሁ” አላት። ሴቲቱም ኢዮአብን፣ “የሰውየው ራስ ተቈርጦ በግንቡ ላይ ይወረወርልሃል” አለችው።See the chapter መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 ነገሩስ እንዲህ አይደለም፤ የኰረብታማው የኤፍሬሙ አገር ሰው፥ የቢክሪ ልጅ ሼባዕ እጁን በንጉሡ በዳዊት ላይ አንሥቶአል፤ እናንተ ይህን ሰው ብቻ ስጡኝ እንጂ እኔ ከተማዪቱን ትቼ እሄዳለሁ” አላት። ሴቲቱም ኢዮአብን፥ “የሰውየው ራስ ተቆርጦ በግንቡ ላይ ይወረወርልሃል” አለችው።See the chapter አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 የእኛ ዕቅድ ይህ አይደለም፤ የተራራማው የኤፍሬም አገር ተወላጅ የሆነ ሼባዕ ተብሎ የሚጠራ የቢክሪ ልጅ በንጉሥ ዳዊት ላይ ዐመፅ አስነሥቶአል፤ ብቻ ይህ ሰው ይሰጠኝ እንጂ እኔ ከተማይቱን ለቅቄ እሄዳለሁ።” እርስዋም “ራሱን ቈርጠን በግንብ ላይ እንወረውርልሃለን” አለችው።See the chapter መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 ነገሩ እንዲህ አይደለም፥ ከተራራማው ከኤፍሬም አገር የሚሆን የቢክሪ ልጅ ሳቤዔ የሚባል አንድ ሰው ግን በንጉሡ በዳዊት ላይ እጁን አነሣ፥ እርሱን ብቻውን ስጡኝ፥ እኔም ከከተማይቱ እርቃለሁ አላት። ሴቲቱም ኢዮአብን፦ እነሆ፥ ራሱ ከቅጥር ላይ ይጣልልሃል አለችው።See the chapter |