2 ሳሙኤል 20:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 አሜሳይም በደም ተነክሮ በመንገድ መካከል ወድቆ ነበር፤ ያም ሰው ወደ እርሱ የሚመጣ ሁሉ ሲቆም አይቶአልና ሕዝቡ ሁሉ እንደ ቆመ ባየ ጊዜ አሜሳይን ከመንገድ ላይ ወደ እርሻ ውስጥ ፈቀቅ አደረገው፤ በልብስም ከደነው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 በዚህ ጊዜ የአሜሳይ ሬሳ በደም ተጨማልቆ በመንገዱ መካከል ወድቆ ነበር፤ በዚያ የሚያልፈው ሰራዊት ሁሉ መቆሙን ያ ሰው አየ፤ ወደ ሬሳው የደረሰው ሰራዊት ሁሉ መቆሙን በተረዳ ጊዜም፣ የአሜሳይን ሬሳ ከመንገድ ወደ ዕርሻ ፈቀቅ አድርጎ ልብስ ጣል አደረገበት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 በዚህን ጊዜ የአማሳይ ሬሳ በደም ተጨማልቆ በመንገዱ መካከል ወድቆ ነበር፤ በዚያ የሚያልፈው ሠራዊት ሁሉ መቆሙን ያ ሰው አየ፤ ወደ ሬሳው የደረሰው ሠራዊት ሁሉ መቆሙን በተረዳ ጊዜም፥ የአማሳይን ሬሳ ከመንገድ ወደ እርሻ ፈቀቅ አድርጎ በልብስ ሸፈነው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 የዐማሳ ሬሳ በደም እንደ ተበከለ በመንገዱ መካከል ተዘርሮ ነበር፤ ያም ሰው የኢዮአብ ወታደር ሁሉ ቆሞ ሲመለከት አይቶ ሬሳውን በመጐተት ወደ እርሻ ወሰደውና በልብስ ሸፈነው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 አሜሳይም በመንገድ መካከል ወድቆ በደሙ ላይ ይንከባለል ነበር፥ ያም ሰው ወደ እርሱ የሚመጣ ሁሉ ሲቆም አይቶአልና ሕዝቡ ሁሉ እንደ ቆመ ባየ ጊዜ አሜሳይን ከመንገድ ላይ ወደ እርሻ ውስጥ ፈቀቅ አደረገው፥ በልብስም ከደነው። See the chapter |