2 ሳሙኤል 2:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)29 አበኔርና ሰዎቹም ሌሊቱን ሁሉ ወደ ምዕራብ ሄዱ፤ ዮርዳኖስንም ተሻገሩ፤ ያን ቀጥተኛ መንገድ ካለፉ በኋላም ወደ ሰፈር መጡ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም29 አበኔርና ሰዎቹም ሌሊቱን ዓረባን ዐልፈው ሄዱ፤ ከዚያም ዮርዳኖስን በመሻገር ቢትሮንን ሁሉ ዐልፈው ወደ መሃናይም መጡ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)29 አበኔርና ሰዎቹም ሌሊቱን ዓራባን አልፈው ሄዱ፤ ዮርዳኖስንም በመሻገር ቢትሮንን ሁሉ ዐልፈው ወደ ማሕናይም መጡ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም29 አበኔርና ሰዎቹ ሌሊቱን ሁሉ በመጓዝ በዓራባ ሸለቆ በኩል ሄዱ፤ ዮርዳኖስንም ተሻግረው በመጓዝ ቢትሮንን ሁሉ ዓልፈው ወደ ማኅናይም መጡ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)29 አበኔርና ሰዎቹም ሌሊቱን ሁሉ ዓረባ እያለፉ ሄዱ፥ ዮርዳኖስንም ተሻገሩ፥ ቢትሮንንም ሁሉ ካለፉ በኋላ ወደ መሃናይም መጡ። See the chapter |