Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 2:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 አበ​ኔ​ርም፥ “ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ፈቀቅ በል፤ ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም አንድ ጐል​ማሳ ያዝ፤ መሣ​ሪ​ያ​ው​ንም ለራ​ስህ ውሰድ” አለው። አሣ​ሄል ግን እር​ሱን ከማ​ሳ​ደድ ፈቀቅ ይል ዘንድ እንቢ አለ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ከዚያም አበኔር፣ “ወደ ቀኝህ ወይም ወደ ግራህ ዘወር በልና አንዱን ጕልማሳ ይዘህ መሣሪያውን ንጠቀው” አለው። አሣሄል ግን እርሱን መከታተሉን አልተወም ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ከዚያም አበኔር፥ “ወደ ቀኝህ ወይም ወደ ግራህ ዘወር በልና አንዱን ጎልማሳ ይዘህ ምርኮውን ውሰድ” አለው። አሣሄል ግን እርሱን ማሳደዱን ቀጠለ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 አበኔርም “እኔን ማሳደድ ተው! ይልቅስ ከወታደሮቹ አንዱን በማሳደድ የያዘውን ምርኮ ውሰድ” አለው፤ ዐሣሄል ግን እርሱን ማሳደዱን ቀጠለ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 አበኔርም፦ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ፈቀቅ በል፥ አንድ ጕልማሳ ያዝ፥ መሣርያውንም ውስድ አለው። አሣሄል ግን እርሱን ከማሳደድ ፈቀቅ ይል ዘንድ እንቢ አለ።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 2:21
3 Cross References  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በላዩ ወረደ፤ ወደ አስ​ቀ​ሎ​ናም ወረደ፤ ከዚ​ያም ሠላሳ ሰዎ​ችን ገደለ፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም ገፍፎ እን​ቆ​ቅ​ል​ሹን ለነ​ገ​ሩት ሰዎች ሰጠ። ሶም​ሶ​ንም ተቈጣ፤ ወደ አባ​ቱም ቤት ተመ​ለሰ።


አበ​ኔ​ርም ወደ ኋላው ተመ​ልሶ፥ “አንተ አሣ​ሄል ነህን?” አለው። እር​ሱም፥ “አዎ፥ እኔ ነኝ” አለው።


አበ​ኔ​ርም አሣ​ሄ​ልን፥ “ከም​ድር ጋር እን​ዳ​ላ​ጣ​ብ​ቅህ እኔን ከማ​ሳ​ደድ ፈቀቅ በል፤ ወደ ወን​ድ​ምህ ወደ ኢዮ​አብ ፊቴን አቅ​ንቼ አይ ዘንድ እን​ዴት ይቻ​ለ​ኛል? እን​ደ​ዚህ አይ​ሆ​ን​ምና ወደ ወን​ድ​ምህ ወደ ኢዮ​አብ ተመ​ለስ” አለው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements