2 ሳሙኤል 2:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 የሶርህያ ልጅ ኢዮአብና የዳዊት ብላቴኖች ከኬብሮን ወጥተው በገባዖን ውኃ መቆሚያ አጠገብ ተገናኙአቸው፤ በውኃውም መቆሚያ በአንዱ ወገን እነዚህ፥ በሌላውም ወገን እነዚያ ሆነው ተቀመጡ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 እነርሱንም የጽሩያ ልጅ ኢዮአብና የዳዊት ሰዎች ወጥተው በገባዖን ኵሬ አጠገብ ተገናኟቸው፤ አንዱ ወገን በኵሬው ወዲህ ማዶ፣ ሌላው ወገን ደግሞ በኵሬው ወዲያ ማዶ ተቀመጠ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 እነርሱንም የጽሩያ ልጅ ኢዮአብና የዳዊት ሰዎች ወጥተው በገባዖን ኲሬ አጠገብ ተገናቿቸው፤ አንዱ ወገን በኲሬው ወዲህ ማዶ፥ ሌላው ወገን ደግሞ በኲሬው ወዲያ ማዶ ተቀመጠ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 እናቱ ጸሩያ ተብላ የምትጠራው ኢዮአብና ሌሎቹም የዳዊት ባለሥልጣኖች ወጥተው በገባዖን ኲሬ ውሃ አጠገብ ተገናኙ፤ ሁሉም በቡድን ተከፋፍለው በኲሬው ውሃ ማዶ ለማዶ ተቀምጠው ነበር። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 የጽሩያ ልጅ ኢዮአብና የዳዊት ባሪያዎች ወጥተው በገባዖን ውኃ መቆሚያ አጠገብ ተገናኙአቸው፥ በውኃውም መቆሚያ በአንዱ ወገን እነዚህ፥ በሌላውም ወገን እነዚያ ሆነው ተቀመጡ። See the chapter |