Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 19:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 ንጉ​ሡም ወደ ጌል​ገላ ተሻ​ገረ፤ ከመ​ዓ​ምም ከእ​ርሱ ጋር ተሻ​ገረ፤ የይ​ሁ​ዳም ሕዝብ ሁሉ፥ ደግ​ሞም የእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ እኩ​ሌታ ከን​ጉሡ ጋር ተሻ​ገሩ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 ንጉሡ ወደ ጌልገላ ሲሄድ፣ ከመዓም ዐብሮት ሄደ። የይሁዳ ሰራዊት በሙሉ እንዲሁም ግማሹ የእስራኤል ሰራዊት ንጉሡን አጅበው አሻገሩት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 ስለዚህም ሕዝቡ በሙሉ ዮርዳኖስን ተሻገረ፤ ንጉሡም ተሻገረ። ንጉሡ ባርዚላይን ስሞ መረቀው፤ ባርዚላይም ወደ ቤቱ ተመለሰ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 ንጉሥ ዳዊት በይሁዳ ሕዝብ ሁሉና በእስራኤል ሕዝብ እኩሌታ ታጅቦ ወንዙን ከተሻገረ በኋላ ወደ ጌልጌላ አቀና፤ ኪምሀምም አብሮት ተሻገረ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 ንጉሡም ወደ ጌልገላ ተሻገረ፥ ከመዓምም ከእርሱ ጋር ሄደ፥ የይሁዳም ሕዝብ ሁሉ ደግሞም የእስራኤል ሕዝብ እኩሌታ ንጉሡን አሻገረው።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 19:40
6 Cross References  

የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው! ሆሣዕና በአርያም!” እያሉ ይጮኹ ነበር።


መን​ግ​ሥት ከይ​ሁዳ አይ​ጠ​ፋም፤ ምስ​ፍ​ናም ከአ​ብ​ራኩ፥ ለእ​ርሱ የሚ​ጠ​ብ​ቀ​ውን እስ​ኪ​ያ​ገኝ ድረስ፤ የአ​ሕ​ዛብ ተስ​ፋ​ቸው እርሱ ነውና፤


ከመ​ላው ነገደ እስ​ራ​ኤል የተ​ሰ​በ​ሰቡ ሕዝብ፥ “ንጉሡ ዳዊት ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን እጅ ታድ​ጎ​ናል፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም እጅ አድ​ኖ​ናል፤ አሁ​ንም ስለ አቤ​ሴ​ሎም ከሀ​ገ​ሩና ከመ​ን​ግ​ሥቱ ሸሸ።


በላ​ያ​ችን ላይ የቀ​ባ​ነው አቤ​ሴ​ሎ​ምም በጦ​ር​ነት ሞቶ​አል፤ አሁ​ንም ንጉ​ሡን ለመ​መ​ለስ ስለ​ምን ዝም ትላ​ላ​ችሁ?” አሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቃል ወደ ንጉሥ ደረሰ።


እኔ ባሪ​ያህ ተመ​ልሼ በከ​ተ​ማዬ በአ​ባ​ቴና በእ​ናቴ መቃ​ብር አጠ​ገብ እባ​ክህ! ልሙት፤ ነገር ግን ባሪ​ያህ ከመ​ዓም ከጌ​ታዬ ከን​ጉሡ ጋር ይሻ​ገር፤ በዐ​ይ​ኖ​ችህ ፊት ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህ​ንም ለእ​ርሱ አድ​ርግ።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements