2 ሳሙኤል 19:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 ከሰልፍ በሸሸ ጊዜ ያፈረ ሕዝብ ተሰርቆ እንደሚገባ በዚያ ቀን ሕዝቡ ተሰርቀው ወደ ከተማ ገቡ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 በዚያችም ዕለት ከጦርነት ሸሽቶ በኀፍረት እየተሸማቀቀ ወደ ከተማ እንደሚገባ ሰው ሕዝቡም ተሸማቆ ወደ ከተማ ገባ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ንጉሡ፥ “ስለ ልጁ አዝኖአል” መባሉን በዚያ ቀን ሠራዊቱ ሰምቶ ስለ ነበር፥ የዚያ ዕለት ድል በመላው ሠራዊት ዘንድ ወደ ኀዘን ተለውጦ ዋለ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 ስለዚህ ከጦር ግንባር ተመልሰው ወደ ኋላ እንደሚሸሹ ወታደሮች ድምፃቸውን አጥፍተው በጸጥታ ወደ ከተማይቱ ገቡ፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 ሕዝቡም ከሰልፍ የሸሸ ሕዝብ አፍሮ ወደ ኋላው እንዲል በዚያ ቀን ወደ ከተማ ተሰርቆ ገባ። See the chapter |