Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 19:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ከእ​ር​ሱም ጋራ ከብ​ን​ያም ወገን የሆኑ ሺህ ሰዎች ነበሩ፤ የሳ​ኦ​ልም ቤት አገ​ል​ጋይ ሲባ ከእ​ር​ሱም ጋር ዐሥራ አም​ስቱ ልጆ​ቹና ሃያው አገ​ል​ጋ​ዮቹ ነበሩ፤ በን​ጉ​ሡም ፊት በቀ​ጥታ ወደ ዮር​ዳ​ኖስ ሄዱ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ከርሱም ጋራ አንድ ሺሕ ብንያማውያን፣ እንዲሁም የሳኦል ቤተ ሰብ አገልጋይ ሲባ ከዐሥራ ዐምስት ወንዶች ልጆቹና ከሃያ አሽከሮቹ ጋራ ሆኖ ዐብረውት ነበሩ። ከዚያም ንጉሡ ወዳለበት ወደ ዮርዳኖስ በጥድፊያ ወረዱ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የባሑሪም ሰው የሆነው የጌራ ልጅ ብንያማዊው ሺምዒ ከይሁዳ ሰዎች ጋር ሆኖ ንጉሥ ዳዊትን ለመቀበል ፈጥኖ ሄደ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ከእርሱም ጋር የብንያም ነገድ የሆኑ አንድ ሺህ ሰዎች ነበሩ፤ የሳኦል ቤተሰብ አገልጋይ የነበረው ጺባም ከዐሥራ አምስት ወንዶች ልጆቹና ከኻያ አገልጋዮቹ ጋር መጣ፤ ወደ ዮርዳኖስም ወንዝ እየተጣደፉ ደርሰው በንጉሡ ፊት ቀረቡ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ከእርሱም ጋር ብንያማውያን የሆኑ ሺህ ሰዎች ነበሩ፥ የሳኦልም ቤት ባሪያ ሲባ ከእርሱም ጋር አሥራ አምስቱ ልጆችና ሀያው ባሪያዎች ነበሩ፥ በንጉሡም ፊት ፈጥነው ዮርዳኖስን ተሻገሩ።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 19:17
8 Cross References  

ከሳ​ኦ​ልም ቤት አንድ ብላ​ቴና ነበረ፤ ስሙም ሲባ ነበረ፤ ወደ ዳዊ​ትም ጠሩት፤ ንጉ​ሡም፥ “አንተ ሲባ ነህን?” አለው። እር​ሱም፥ “እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ነኝ” አለ።


አን​ተና ልጆ​ችህ፥ ሎሌ​ዎ​ች​ህም ምድ​ሩን እረ​ሱ​ለት፤ ለጌ​ታ​ህም ልጅ እን​ጀራ ይሆ​ነው ዘንድ ፍሬ​ውን አግቡ፤ እና​ን​ተም ትመ​ግ​ቡ​ታ​ላ​ችሁ፤የጌ​ታህ ልጅ ሜም​ፌ​ቡ​ስቴ ግን ሁል​ጊዜ ከገ​በ​ታዬ ይበ​ላል” አለው። ለሲ​ባም ዐሥራ አም​ስት ልጆ​ችና ሃያ አገ​ል​ጋ​ዮች ነበ​ሩት።


ንጉ​ሡ​ንም የማ​ሻ​ገር ሥራ ሠሩ። የን​ጉ​ሡ​ንም ቤተ ሰብእ ያነሡ ዘንድ፥ በፊ​ቱም የቀና ሥራን ይሠሩ ዘንድ ወደ ማዶ ተሻ​ገሩ። ንጉ​ሡም ዮር​ዳ​ኖ​ስን ከተ​ሻ​ገረ በኋላ የጌራ ልጅ ሳሚ በን​ጉሡ ፊት፦ በግ​ን​ባሩ ወደቀ።


ባል​ዋም እያ​ለ​ቀሰ ከእ​ር​ስዋ ጋር ሄደ፤ እስከ ብራ​ቂም ድረስ ተከ​ተ​ላት። አበ​ኔ​ርም፥ “ሂድ፤ ተመ​ለስ” አለው፤ እር​ሱም ተመ​ለሰ።


ንጉሡ ዳዊ​ትም ወደ በው​ሪም መጣ፤ እነ​ሆም፥ ሳሚ የሚ​ባል የጌራ ልጅ ከሳ​ኦል ቤተ ዘመድ የሆነ አንድ ሰው ከዚያ ወጣ፤ እየ​ሄ​ደም ይረ​ግ​መው ነበር።


የባ​ው​ሬም ሀገር ሰው የብ​ን​ያ​ማ​ዊው የጌራ ልጅ ሳሚ እነሆ! በአ​ንተ ዘንድ ነው፤ እኔም ወደ መሃ​ና​ይም በሄ​ድሁ ጊዜ ብርቱ ርግ​ማን ረገ​መኝ፤ ከዚ​ያም በኋላ ዮር​ዳ​ኖ​ስን በተ​ሻ​ገ​ርሁ ጊዜ ሊቀ​በ​ለኝ ወረደ፤ እኔም፦ ‘በሰ​ይፍ አል​ገ​ድ​ል​ህም’ ብዬ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምየ​ለ​ታ​ለሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements