Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 18:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 እነ​ሆም፥ ኩሲ መጣ፤ ኩሲም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላ​ይህ የተ​ነ​ሡ​ትን ሁሉ ዛሬ እንደ ተበ​ቀ​ለ​ልህ ለጌ​ታዬ ለን​ጉሡ ወሬ አም​ጥ​ቻ​ለሁ” አለ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ከዚያም ኢትዮጵያዊው ደርሶ፣ “ንጉሥ ጌታዬ ሆይ፤ የምሥራች! ዛሬ እግዚአብሔር ከተነሡብህ ጠላቶችህ ሁሉ ታድጎሃል” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ከዚያም ኢትዮጵያዊው ደርሶ፥ “ንጉሥ ጌታዬ ሆይ፤ የምሥራች! ዛሬ ጌታ ከተነሡብህ ጠላቶችህ ሁሉ ታድጎሃል” አለው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ቀጥሎም ኢትዮጵያዊው አገልጋይ እዚያ ደረሰና ንጉሡን “ንጉሥ ሆይ! የምሥራች ቃል ይዤልህ መጥቼአለሁ፤ በአንተ ላይ በዐመፅ የተነሣሡብህን ድል እንድታደርግ ዛሬ እግዚአብሔር ረድቶሃል!” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 እነሆም፥ ኵሲ መጣ፥ ኵሲም፦ እግዚአብሔር በላይህ የተነሡትን ሁሉ ዛሬ እንደ ተበቀለልህ ለጌታዬ ለንጉሡ ወሬ አምጥቼአለሁ አለ።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 18:31
11 Cross References  

የሳ​ዶቅ ልጅ አኪ​ማ​ሖስ ግን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጠ​ላ​ቶቹ እጅ እንደ ፈረ​ደ​ለት ፈጥኜ ሄጄ ለን​ጉሥ የም​ሥ​ራች ልን​ገ​ርን?” አለ።


የአ​ም​ላኬ ይቅ​ር​ታው ይድ​ረ​ሰኝ አም​ላኬ በጠ​ላ​ቶቼ ላይ አሳ​የኝ።


አኪ​ማ​ሖ​ስም ጮኾ ንጉ​ሡን፥ “ሰላም ለአ​ንተ ይሁን!” አለው። በን​ጉ​ሡም ፊት በም​ድር ላይ በግ​ን​ባሩ ሰግዶ፥ “በን​ጉሡ በጌ​ታዬ ላይ እጃ​ቸ​ውን ያነ​ሡ​ትን ሰዎች አሳ​ልፎ የሰጠ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን” አለ።


አቤቱ ጠላ​ቶ​ችህ ሁሉ እን​ዲሁ ይጥፉ፤ ወዳ​ጆ​ችህ ግን ፀሐይ በኀ​ይሉ በወጣ ጊዜ እን​ደ​ሚ​ሆን፤ እን​ዲሁ ይሁኑ። ምድ​ሪ​ቱም አርባ ዓመት ያህል ዐረ​ፈች።


ንጉ​ሡም፥ “ፈቀቅ ብለህ ቁም” አለ፤ እር​ሱም ፈቀቅ ብሎ ቆመ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements