Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 18:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ዳዊ​ትም በሁ​ለት በር መካ​ከል ተቀ​ምጦ ነበር፤ ዘበ​ኛ​ውም በቅ​ጥሩ ላይ ወዳ​ለው ወደ በሩ ሰገ​ነት ወጣ፤ ዐይ​ኑ​ንም አቅ​ንቶ ብቻ​ውን የሚ​ሮጥ ሰው አየ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ዳዊት በውስጠኛውና በውጭኛው በሮች መካከል ተቀምጦ ሳለ፣ ጠባቂው ቅጥሩ ላይ ወዳለው ወደ በሩ ሰገነት ጣራ ወጥቶ ወደ ውጭ ሲመለከት፣ አንድ ሰው ብቻውን ሲሮጥ አየ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ዳዊት በውስጠኛውና በውጭኛው በሮች መካከል ተቀምጦ ነበር፤ ጠባቂውም ቅጥሩ ላይ ወዳለው ወደ በሩ ሰገነት ጣራ ወጣ፤ ቀና ብሎም ሲመለከት አንድ ሰው ብቻውን እየሮጠ ሲመጣ አየ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ዳዊት በከተማይቱ ውስጣዊና ውጫዊ በሮች መካከል ባለው ግልጥ ቦታ ተቀምጦ ነበር፤ ጠባቂው በቅጥሩ በኩል ወደ ማማው ወጥቶ ስለ ነበር ቀና ብሎ ሲመለከት አንድ ሰው ብቻውን እየሮጠ ሲመጣ አየ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ዳዊትም በሁለት በር መካከል ተቀምጦ ነበር፥ ዘበኛውም በቅጥሩ ላይ ወዳለው ወደበሩ ሰገነት ወጣ፥ አይኑንም አቅንቶ ብቻውን የሚሮጥ ሰው አየ።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 18:24
10 Cross References  

ንጉ​ሡም ተነ​ሥቶ በበሩ ተቀ​መጠ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ንጉሡ በበሩ ተቀ​ም​ጧል ብለው ተና​ገሩ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ በበሩ ወደ ንጉሡ ፊት ወጡ። እስ​ራ​ኤ​ልም እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ድን​ኳኑ ሸሽቶ ገብቶ ነበር።


ንጉ​ሡም፥ “በፊ​ታ​ችሁ መል​ካም የሚ​መ​ስ​ላ​ች​ሁን አደ​ር​ጋ​ለሁ” አላ​ቸው። ንጉ​ሡም በበሩ አጠ​ገብ ቆመ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ መቶ በመቶ፥ ሺህ በሺህ እየ​ሆኑ ወጡ።


አቤ​ሴ​ሎ​ምም ኰበ​ለለ። ጕበ​ኛ​ውም ጐል​ማሳ ዐይ​ኑን ከፍ አደ​ረገ፤ እነ​ሆም፥ ብዙ ሰዎች በኋ​ላው በተ​ራ​ራው አጠ​ገብ በመ​ን​ገድ ሲመጡ አየ። ጕበ​ኛ​ውም መጥቶ ለን​ጉሡ እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥ “ብዙ ሰዎች በተ​ራ​ራው ጎን ባለው በአ​ር​ኖን መን​ገድ ሲመጡ አየሁ።”


በመ​ጣም ጊዜ ዔሊ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ልቡ ተና​ውጦ ነበ​ርና በመ​ን​ገድ ዳር በወ​ን​በሩ ላይ ተቀ​ምጦ ይጠ​ባ​በቅ ነበር፤ ሰው​ዬ​ውም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ገብቶ ባወራ ጊዜ ከተ​ማ​ዪቱ ሁሉ ተጭ​ዋ​ጭ​ዋ​ኸች።


እር​ሱም፥ “እኔ ብሮጥ ምን ይገ​ድ​ዳል?” አለ። እር​ሱም፥ “ሩጥ” አለው። አኪ​ማ​ሖ​ስም በሰ​ርጥ ጎዳና በኩል ሮጠ፤ ኩሲ​ንም ቀደ​መው።


ዘበ​ኛ​ውም ለን​ጉሡ ሊነ​ግ​ረው ጮኸ። ንጉ​ሡም፥ “ብቻ​ውን እንደ ሆነ በአፉ ወሬ ይኖ​ራል” አለ። እር​ሱም ፈጥኖ ቀረበ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements