2 ሳሙኤል 18:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 ሰውየውም ኢዮአብን፥ “ንጉሡ አንተንና አቢሳን፥ ኤቲንም፦ ብላቴናውን አቤሴሎምን ጠብቁ ብሎ ሲያዝ እኛ በጆሮአችን ሰምተናልና ሺህ ሰቅል ብር በእጄ ላይ ብትመዝን እጄን በንጉሡ ልጅ ላይ አልዘረጋም ነበር። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 ሰውየው ግን ለኢዮአብ እንዲህ አለው፤ “እኛ እየሰማን ንጉሡ፣ ‘ወጣቱ አቤሴሎም ጕዳት እንዳያገኘው ስለ እኔ ብላችሁ ጠብቁት’ ብሎ አንተን፣ አቢሳንና ኢታይን ያዘዛችሁ ስለ ሆነ፣ አንድ ሺሕ ሰቅል ጥሬ ብር በእጄ ላይ ቢመዘንልኝ እንኳ፣ በንጉሡ ልጅ ላይ እጄን አላነሣም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 ሰውየው ግን ለኢዮአብ እንዲህ አለ፤ “እኛ እየሰማን ንጉሡ፥ ‘ወጣቱ አቤሴሎም ጉዳት እንዳያገኘው ስለ እኔ ብላችሁ ጠብቁት’ ተብሎ አንተን፥ አቢሳንና ኢታይን ያዘዛችሁ ስለሆነ፥ አንድ ሺህ ብር በእጄ ላይ ቢመዘንልኝ እንኳ፥ በንጉሡ ልጅ ላይ እጄን አላነሣም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 ሰውየው ግን እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አንድ ሺህ ጥሬ ብር እንኳ ብትሰጠኝ በንጉሡ ልጅ ላይ እጄን አላነሣም፤ ንጉሡ ለአንተ፥ ለአቢሳና ለኢታይ ‘ለእኔ ስትሉ በወጣቱ አቤሴሎም ላይ ለሞት የሚያደርስ ጒዳት እንዳታደርሱበት’ ሲል የሰጣችሁን ትእዛዝ ሁላችንም ሰምተናል፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 ሰውዮውም ኢዮአብን፦ እኛ ስንሰማ ንጉሡ አንተንና አቢሳን ኢታይንም፦ ብላቴናውን አቤሴሎምን ማንም እንዳይነካው ተጠንቀቁ ብሎ አዝዞአልና ሺህ ብር በእጄ ላይ ብትመዝን እጄን በንጉሡ ልጅ ላይ ባልዘረጋሁም ነበር አለው። See the chapter |