2 ሳሙኤል 18:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ኢዮአብም ለነገረው ሰው፥ “እነሆ፥ ካየኸው ለምን በምድር ላይ አልገደልኸውም? ዐሥር ብርና አንድ ድግ እሰጥህ ነበር” አለው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ኢዮአብም ይህን የነገረውን ሰው፣ “ምን አልህ! ካየኸው ታዲያ ለምንድን ነው ያኔውኑ መትተህ መሬት ላይ ያልጣልኸው? ይህን አድርገህ ቢሆን ኖሮ፣ ዐሥር ሰቅል ጥሬ ብርና የጀግና ሰው ቀበቶም እሸልምህ ነበር” አለው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ኢዮአብም ይህን የነገረውን ሰው፥ “ምን አልህ! ካየኸው ታዲያ ለምንድን ነው ያኔውኑ መተህ ምድር ላይ ያልጣልኸው? ይህን አድርገህ ቢሆን ኖሮ፥ ዐሥር ብርና ዝናር እሸልምህ ነበር” አለው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ኢዮአብም “ታዲያ ካየኸው ለምን ወዲያውኑ አልገደልከውም? ይህን አድርገህ ቢሆን ኖሮ እኔ ራሴ ዐሥር ጥሬ ብርና አንድ ዙር ዝናር በሸለምኩህ ነበር” ሲል መለሰለት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ኢዮአብም ለነገረው ሰው፦ እነሆ፥ ካየኸው ለምን ወደ ምድር አልመታኸውም? አሥር ብርና አንድ ድግ እሰጥህ ነበር አለው። See the chapter |