2 ሳሙኤል 17:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ኩሲም ወደ አቤሴሎም በመጣ ጊዜ አቤሴሎም፥ “አኪጦፌል ያለው ይህ ነው፤ ነገሩን እናደርገው ዘንድ ይገባልን? ባይሆን ግን አንተ ንገረን” ብሎ ተናገረው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ኩሲ ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ አቤሴሎም፣ “አኪጦፌል ይህን ምክር አቅርቧል፤ ታዲያ እርሱ ያለውን እናድርግ? ካልሆነም እስኪ የአንተን ሐሳብ ንገረን” አለው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ሑሻይም ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ አቤሴሎም፥ “አኪጦፌል ይህን ምክር አቅርቧል፤ ታዲያ የእርሱን ምክር እንከተል? ካልሆነ እስቲ አንተ ተናገር” አለው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ሑሻይም በደረሰ ጊዜ አቤሴሎም “አኪጦፌል የሰጠን ምክር ይህ ነው፤ ይህንኑ ምክር እንከተል ወይስ ምን ማድረግ እንደሚገባን አንተም የምትነግረን አለ ይሆን?” ሲል ጠየቀው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ኩሲም ወደ አቤሴሎም በመጣ ጊዜ አቤሴሎም፦ አኪጦፌል ያለው ይህ ነው፥ ነገሩን እናደርገው ዘንድ ይገባልን? ባይሆን ግን አንተ ንገረን ብሎ ተናገረው። See the chapter |