2 ሳሙኤል 17:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 የአቤሴሎምም አገልጋዮች ወደ ሴቲቱ ወደ ቤት መጥተው፥ “አኪማሆስና ዮናታን የት አሉ?” አሉ፤ ሴቲቱም፥ “ፈፋውን ተሻግረው ሄዱ፤ ጥቂትም ቀደሙአችሁ” አለቻቸው። እነርሱም ፈልገው አጡአቸው፤ ወደ ኢየሩሳሌምም ተመለሱ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም20 የአቤሴሎም ሰዎች እዚያ ቤት ወደ ሴቲቱ ዘንድ መጥተው፣ “አኪማአስና ዮናታን የት አሉ?” ብለው ጠየቁ። ሴቲቱም፣ “ወንዙን ተሻግረው ሄደዋል” ብላ መለሰችላቸው፤ እነርሱም ፈልገው ስላጧቸው፣ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 የአቤሴሎም ሰዎች እዚያ ቤት ወደ ሴቲቱ ዘንድ መጥተው፥ “አሒማዓጽና ዮናታን የት አሉ?” ብለው ጠየቋት። ሴቲቱም፥ “ወንዙን ተሻግረው ሄደዋል” ብላ መለሰችላቸው፤ እነርሱም ፈልገው ስላጧቸው፥ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 የአቤሴሎም ባለሟሎች ወደዚያ ቤት መጥተው ሴቲቱን “አሒማዓጽና ዮናታን የት ናቸው?” ሲሉ ጠየቁአት። እርስዋም “ወንዙን ተሻግረው ሄደዋል” ስትል መለሰች። ሰዎቹም ፈልገው ሊያገኙአቸው ስላልቻሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 የአቤሴሎም ባሪያዎች ወደ ሴቲቱ ወደ ቤት መጥተው፦ አኪማአስና ዮናታን የት አሉ? አሉ፥ ሴቲቱም፦ ፈፋውን ተሻግረው ሄዱ አለቻቸው። እነርሱም ፈልገው ባላገኙአቸው ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። See the chapter |