Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 16:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 የዳ​ዊ​ትም ወዳጅ ኩሲ ወደ አቤ​ሴ​ሎም በመጣ ጊዜ ኩሲ አቤ​ሴ​ሎ​ምን፥ “ንጉሥ ሆይ! ሽህ ዓመት ያን​ግ​ሥህ” አለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 የዳዊት ወዳጅ አርካዊው ኩሲም ወደ አቤሴሎም መጥቶ “ንጉሥ ሆይ፤ ለዘላለም ንገሥ፤ ንጉሥ ሆይ፤ ለዘላለም ንገሥ” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 የዳዊት ወዳጅ አርካዊው ሑሻይም ወደ አቤሴሎም መጥቶ “ንጉሥ ሆይ፤ ለዘለዓለም ንገሥ፤ ንጉሥ ሆይ፤ ለዘለዓለም ንገሥ” አለው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 የዳዊት ታማኝ ወዳጅ ሑሻይ አቤሴሎምን ባገኘው ጊዜ “ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ! ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ! ይሁን!” እያለ ጮኸ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 የዳዊትም ወዳጅ አርካዊው ኩሲ ወደ አቤሴሎም በመጣ ጊዜ ኩሲ፦ ሺህ ዓመት ያንግሥህ አለው።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 16:16
13 Cross References  

የን​ጉ​ሡ​ንም ልጅ አው​ጥቶ ዘው​ዱን ጫነ​በት፤ ምስ​ክ​ሩ​ንም ሰጠው፤ ቀብ​ቶም አነ​ገ​ሠው፥ “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይን​ገሥ” እያሉ በእ​ጃ​ቸው አጨ​በ​ጨቡ።


ሳሙ​ኤ​ልም ለሕ​ዝቡ ሁሉ፥ “ከሕ​ዝቡ ሁሉ እር​ሱን የሚ​መ​ስል እንደ ሌለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ረ​ጠ​ውን ታያ​ላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ፥ “ንጉሥ ሕያው ይሁን” እያሉ እል​ልታ አደ​ረጉ።


እርሱ ዛሬ ወርዶ ብዙ በሬ​ዎ​ች​ንና ጠቦ​ቶ​ችን፥ በጎ​ች​ንም ሠው​ቶ​አል፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ልጆች ሁሉ፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱን አለቃ ኢዮ​አ​ብን፥ ካህ​ኑ​ንም አብ​ያ​ታ​ርን ጠር​ቶ​አል፤ እነ​ሆም፥ በፊቱ እየ​በ​ሉና እየ​ጠጡ፦ አዶ​ን​ያስ ሺህ ዓመት ይን​ገሥ ይላሉ።


የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው! ሆሣዕና በአርያም!” እያሉ ይጮኹ ነበር።


በዚ​ያም ካህኑ ሳዶ​ቅና ነቢዩ ናታን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ቀብ​ተው ያን​ግ​ሡት፤ መለ​ከ​ትም ነፍ​ታ​ችሁ፦ ሰሎ​ሞን ሺህ ዓመት ይን​ገሥ በሉ።


የዳ​ዊ​ትም ወዳጅ ኩሲ ወደ ከተማ መጣ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም ደግሞ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ገባ።


ወደ ከተማ ግን ተመ​ል​ሰህ ለአ​ቤ​ሴ​ሎም፦ ወን​ድ​ሞ​ችህ፥ ንጉ​ሡም መጡ። እነሆ፥ በኋ​ላዬ ናቸው። ንጉሥ ሆይ፥ አገ​ል​ጋ​ይህ ነኝ፤ አስ​ቀ​ድሞ ለአ​ባ​ትህ አገ​ል​ጋይ ነበ​ርሁ፥ እን​ዲሁ አሁ​ንም ለአ​ንተ አገ​ል​ጋይ ነኝ፥ ተወኝ ልኑር ብት​ለው የአ​ኪ​ጦ​ፌ​ልን ምክር ትለ​ው​ጥ​ል​ኛ​ለህ።


ዳዊ​ትም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ሰገ​ደ​በት ወደ ተራ​ራው ራስ መጣ፤ ወዳጁ ኵሲም ልብ​ሱን ቀደደ፤ በራ​ሱም ላይ ትቢያ ነስ​ንሶ ሊገ​ና​ኘው መጣ።


የና​ታ​ንም ልጅ ኦርኒያ የሹ​ሞች አለቃ ነበረ፤ የና​ታ​ንም ልጅ ዘባት የን​ጉሡ አማ​ካ​ሪና ወዳጅ ነበረ፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements