2 ሳሙኤል 16:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 ዳዊትም ከተራራው ራስ ጥቂት እልፍ አለ። እነሆም፥ የሜምፌቡስቴ አገልጋይ ሲባ ሁለት መቶ እንጀራ፥ አንድ መቶም ዘለላ ዘቢብ፥ አንድ መቶም ተምር፥ አንድ አቁማዳም ወይን ጠጅ የተጫኑ ሁለት አህዮች እየነዳ ተገናኘው። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 ዳዊት ከተራራው ጫፍ ባሻገር ጥቂት ዕልፍ ብሎ እንደ ሄደ፣ ሲባ የተባለው የሜምፊቦስቴ አገልጋይ፣ ሁለት መቶ እንጀራ፣ አንድ መቶ ጥፍጥፍ ዘቢብ፣ አንድ መቶ ጥፍጥፍ በለስና አንድ አቍማዳ የወይን ጠጅ የተጫኑ ሁለት አህዮች እየነዳ ሊገናኘው መጣ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ዳዊት ከተራራው ጫፍ ባሻገር ጥቂት እልፍ ብሎ እንደ ሄደ፥ ጺባ የተባለው የመፊቦሼት አገልጋይ፥ ሁለት መቶ ሙልሙል ዳቦ፥ አንድ መቶ ጥፍጥፍ ዘቢብ፥ አንድ መቶ እስር ፍራፍሬና አንድ አቁማዳ የወይን ጠጅ የተጫኑ ሁለት አህዮች እየነዳ ሊያገኘው መጣ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 ዳዊት ከኮረብታው ጫፍ ባሻገር ገና ጥቂት እንደ ሄደ ጺባ ተብሎ የሚጠራው የመፊቦሼት አገልጋይ በድንገት አገኘው፤ እርሱም ሁለት መቶ ሙልሙል ዳቦ፥ አንድ መቶ የዘቢብ ጥፍጥፍ፥ አንድ መቶ እስር ፍራፍሬና በወይን ጠጅ የተሞላ አንድ አቁማዳ የተጫኑ ሁለት አህዮች ይነዳ ነበር፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ዳዊትም ከተራራው ራስ ጥቂት ፈቀቅ ባለ ጊዜ የሜምፊቦስቴ ባሪያ ሲባ ሁለት መቶ እንጀራ፥ አንድ መቶም ዘለላ ዘቢብ፥ አንድ መቶም በለስ፥ አንድ አቁማዳም ወይን ጠጅ የተጫኑ ሁለት አህዮች እየነዳ ተገናኘው። See the chapter |