Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 15:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 አቤ​ሴ​ሎ​ምም መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ሠ​ዋ​በት ጊዜ የዳ​ዊት አማ​ካሪ ወደ ነበ​ረው ጌሎ​ና​ዊው አኪ​ጦ​ፌል ወደ ከተ​ማው ጊሎ ላከ። ሴራ​ውም ጽኑ ሆነ፤ ከአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምም ጋር ያለው ሕዝብ እጅግ በዛ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 አቤሴሎም መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ የዳዊት አማካሪ የሆነው የጊሎን ሰው አኪጦፌል ከአገሩ ከጊሎ ወደ እርሱ እንዲመጣ ላከበት፤ ስለዚህ ሤራው ጥንካሬ አገኘ፤ የአቤሴሎምም ተከታዮች ቍጥር እየጨመረ መጣ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 አቤሴሎም መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ የዳዊት አማካሪ የሆነው ጊሎአዊው አኪጦፌል ከአገሩ ከጊሎ ወደ እርሱ እንዲመጣ ላከበት፤ ስለዚህ ሤራው ጥንካሬ አገኘ፤ የአቤሴሎምም ተከታዮች ቍጥር እየበዛ ሄደ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 አቤሴሎም መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ ከንጉሥ ዳዊት አማካሪዎች አንዱ የሆነውን አኪጦፌል ተብሎ የሚጠራውን ሰው መልእክተኛ በመላክ ከጊሎ ከተማ አስጠራ፤ በንጉሡ ላይ የተጠነሰሰው ሤራ እየጠነከረ፥ የአቤሴሎምም ተከታዮች ቊጥር እየጨመረ ሄደ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 አቤሴሎምም የዳዊት መካር የነበረውን የጊሎ ሰው አኪጦፌልን ከከተማው ከጊሎ መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ አስጠራው። ሴራውም ጽኑ ሆነ፥ ከአቤሴሎምም ጋር ያለውች ሕዝብ እየበዛ ሄደ።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 15:12
26 Cross References  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ሁት፥ “አንተ አም​ላኬ ነህ፤ ለምን ረሳ​ኸኝ? ጠላ​ቶቼ ሲያ​ስ​ጨ​ን​ቁኝ ለምን ተው​ኸኝ? ለም​ንስ አዝኜ እመ​ለ​ሳ​ለሁ?” ጠላ​ቶቼ ሁሉ አጥ​ን​ቶ​ቼን እየ​ቀ​ለ​ጣ​ጠሙ ሰደ​ቡኝ።


አኪ​ጦ​ፌል ከአ​ቤ​ሴ​ሎም ጋር በሴራ አንድ ነው ብለው ለዳ​ዊት ነገ​ሩት፤ ዳዊ​ትም፥ “አቤቱ የአ​ኪ​ጦ​ፌ​ልን ምክር ለውጥ” አለ።


ጎሶም ከሉም፥ ከናም፥ ዐሥራ አንድ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።


አኪ​ጦ​ፌ​ልም ምክሩ እን​ዳ​ል​ሠራ ባየ ጊዜ አህ​ያ​ውን ጫነ፤ ተነ​ሥ​ቶም ወደ ቤቱ ወደ ከተ​ማው ሄደ፤ ቤቱ​ንም አደ​ራ​ጅቶ በገዛ እጁ ታንቆ ሞተ፤ በአ​ባ​ቱም መቃ​ብር ተቀ​በረ።


አቤ​ሴ​ሎ​ምና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ “የአ​ር​ካ​ዊው የኩሲ ምክር ከአ​ኪ​ጢ​ፌል ምክር ይሻ​ላል” አሉ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ቤ​ሴ​ሎም ላይ ክፉ ያመጣ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​ካ​ሚ​ቱን የአ​ኪ​ጦ​ፌ​ልን ምክር እን​ዲ​በ​ትን አዘዘ።


እግዚአብሔርን እንዲያውቁ በግልጥ ይናገራሉ፤ ዳሩ ግን የሚያስጸይፉና የማይታዘዙ ለበጎ ሥራም ሁሉ የማይበቁ ስለ ሆኑ፥ በሥራቸው ይክዱታል።


ነገር ግን ይህን የም​ና​ገር ስለ ሁላ​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ የመ​ረ​ጥ​ኋ​ቸው እነ​ማን እንደ ሆኑ እኔ አው​ቃ​ለሁ፤ ነገር ግን መጽ​ሐፍ ‘እን​ጀ​ራ​ዬን የሚ​መ​ገብ ተረ​ከ​ዙን በእኔ ላይ አነሣ’ ያለው ይፈ​ጸም ዘንድ ነው።


የኃጥኣን መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ በክፋት ያቀርቡታልና።


አኪ​ጦ​ፌ​ልም የን​ጉሡ አማ​ካሪ ነበረ። አር​ካ​ዊው ኩሲም የን​ጉሡ አን​ደኛ ወዳጅ ነበረ፤


ከዚ​ህም በኋላ ይህን ነገር በሰማ ጊዜ አብ​ረ​ውት ካሉት ከነ​ገ​ሥ​ታቱ ሁሉ ጋር በድ​ን​ኳኑ ውስጥ ይጠጣ ነበር፤ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንም፥ “ከተ​ማ​ውን እጠ​ሩት” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም በከ​ተ​ማ​ዪቱ ትይዩ ተሰ​ለፉ።


ለወ​ልደ አዴር መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም፥ “ለጌ​ታ​ችሁ፦ ለእኔ አገ​ል​ጋ​ይህ በመ​ጀ​መ​ሪያ የላ​ክ​ህ​ብ​ኝን ሁሉ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ይህን ነገር ግን አደ​ር​ገው ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ኝም” በሉት አላ​ቸው። መል​ክ​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም ተመ​ል​ሰው ይህን ነገር ነገ​ሩት።


ባላ​ቅም በለ​ዓም እን​ዳ​ለው አደ​ረገ፤ በየ​መ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ አንድ ወይ​ፈ​ንና አንድ አውራ በግ አሳ​ረገ።


በሜዳ ወደ ተገ​ነባ ግንብ ራስ ላይም ወሰ​ደው፤ አዞ​ረ​ውም፤ ሰባ​ትም መሠ​ዊ​ያ​ዎች ሠራ፤ በየ​መ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ አንድ ወይ​ፈን፥ አን​ድም አውራ በግ አሳ​ረገ።


በለ​ዓ​ምም ባላ​ቅን፥ “ሰባት መሠ​ዊያ በዚህ ሥራ​ልኝ፤ ሰባ​ትም ወይ​ፈን፥ ሰባ​ትም አውራ በግ በዚህ አዘ​ጋ​ጅ​ልኝ” አለው።


አቤ​ሴ​ሎ​ምና የእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ሁሉ፥ አኪ​ጦ​ፌ​ልም ከእ​ርሱ ጋር ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጡ።


የመ​ካኪ ልጅ የአ​ሶብ ልጅ ኤላ​ፍ​ላት፥ የጊ​ሎ​ና​ዊው የአ​ኪ​ጦ​ፌል ልጅ ኤል​ያብ፥


ሁል​ጊዜ፥ “አም​ላ​ክህ ወዴት ነው?” ይሉ​ኛ​ልና።


የክፉዎች መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ የረከሰ ነው፤ የቅኖች ጸሎት ግን በእርሱ ዘንድ የተወደደ ነው።


ስለ ምንስ ከሳባ ዕጣ​ንን፥ ከሩ​ቅም ሀገር ቀረ​ፋን ታቀ​ር​ቡ​ል​ኛ​ላ​ችሁ? የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን አል​ቀ​በ​ለ​ውም፤ ቍር​ባ​ና​ች​ሁም ደስ አያ​ሰ​ኘ​ኝም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements