Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 14:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እነ​ሆም፥ ዘመ​ዶች ሁሉ በባ​ሪ​ያህ ላይ ተነሡ፤ ስለ ገደ​ለው ስለ ወን​ድሙ ነፍስ እን​ገ​ድ​ለው ዘንድ ወን​ድ​ሙን የገ​ደ​ለ​ውን አውጪ አሉኝ፤ እን​ዲ​ሁም ደግሞ ለባሌ ስምና ዘር በም​ድር ላይ እን​ዳ​ይ​ቀር ወራ​ሹን የቀ​ረ​ውን መብ​ራ​ቴን ያጠ​ፋሉ፤”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እነሆ ቤተ ዘመዱ ሁሉ በባሪያህ ላይ ተነሥተው፣ ‘ወንድሙን ስለ ገደለ እንገድለዋለንና ወንድሙን የገደለውን ሰው አሳልፈሽ ስጪን፣ ከዚያም ወራሽ አልባ ትሆኛለሽ’ ይሉኛል፤ ስለዚህ የቀረኝን አንዱን መብራቴን አጥፍተው፣ ባሌን በምድር ላይ ያለ ስምና ያለ ዘር ሊያስቀሩት ነው።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እነሆ ዘመዶቼ ሁሉ በአገልጋይህ ላይ ተነሥተው፥ ‘ወንድሙን የገደለውን ሰው አሳልፈሽ ስጪን፥ ወራሽ እንኳ ብናጠፋ ወንድሙን ስለ ገደለ እንገድለዋለን’ ይሉኛል፤ ስለዚህ የቀረኝን አንዱን መብራቴን በማጥፋት፥ ባሌን በምድር ላይ ያለ ስምና ያለ ዘር ሊያስቀሩት ነው።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ንጉሥ ሆይ! እነሆ አሁን ዘመዶቼ ሁሉ በእኔ በአገልጋይህ ላይ ተነሥተው ‘ወንድሙን ስለ ገደለ ወራሽ እንኳ ብናጠፋ እንገድለው ዘንድ ወንድሙን የገደለውን ሰው ስጪን’ እያሉ አስቸገሩኝ። ታዲያ፥ እንዲህ የሚያደርጉ ከሆነ የቀረኝን አንድ ተስፋ ሊያጠፉብኝና በምድርም ላይ የባሌን ስምና ዘር ሊያሳጡ ነው።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እነሆም፥ ዘመዶች ሁሉ በባሪያህ ላይ ተነሥተው፦ ስለ ገደለው ስለ ወንድሙ ነፍስ እንገድለው ዘንድ ወንድሙን የገደለውን አውጪ አሉኝ፥ እንዲሁም ደግሞ ወራሹን የቀረውን መብራቴን ያጠፋሉ፥ የባሌን ስምና ዘርም ከምድር ላይ አያስቀሩም።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 14:7
9 Cross References  

ደም ተበ​ቃዩ ራሱ ነፍሰ ገዳ​ዩን ይግ​ደል፤ ባገ​ኘው ጊዜ ይግ​ደ​ለው።


ገበሬዎቹ ግን ልጁን ባዩ ጊዜ እርስ በርሳቸው ‘ወራሹ ይህ ነው፤ ኑ፤ እንግደለውና ርስቱን እናግኝ፤’ ተባባሉ።


የቤ​ቱም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ተነ​ሥ​ተው ከም​ድር ያነ​ሡት ዘንድ በአ​ጠ​ገቡ ቆሙ፤ እርሱ ግን እንቢ አለ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር እን​ጀራ አል​በ​ላም።


የም​ዋቹ ስም ከእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ እን​ዳ​ይ​ጠፋ ከእ​ር​ስዋ የሚ​ወ​ለ​ደው ልጅ በሞ​ተው በወ​ን​ድሙ ስም ይጠራ።


ያደ​ረ​ግ​ህ​በ​ት​ንም እስ​ኪ​ረ​ሳው ድረስ፤ በአ​ንድ ቀን ሁለ​ታ​ች​ሁን እን​ዳ​ላጣ፥ ከዚ​ያም ልኬ አመ​ጣ​ሃ​ለሁ።”


እነሆ፥ ዛሬ ከም​ድር ፊት ከአ​ሳ​ደ​ድ​ኸኝ፥ ከፊ​ትህ እሰ​ወ​ራ​ለሁ፤ በም​ድ​ርም ላይ ኮብ​ላ​ይና ተቅ​በ​ዝ​ባዥ እሆ​ና​ለሁ፤ የሚ​ያ​ገ​ኘ​ኝም ሁሉ ይገ​ድ​ለ​ኛል።”


ለእ​ኔም ለአ​ገ​ል​ጋ​ይህ ሁለት ወን​ዶች ልጆች ነበ​ሩኝ፤ በሜ​ዳም ተጣሉ፤ የሚ​ገ​ላ​ግ​ላ​ቸ​ውም አል​ነ​በ​ረም፤ አን​ዱም ሌላ​ውን መትቶ ገደ​ለው።


ንጉ​ሡም ሴቲ​ቱን፥ “ወደ ቤትሽ በሰ​ላም ሂጂ፤ እኔም ስለ አንቺ አዝ​ዛ​ለሁ” አላት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements