Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 14:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ኢዮ​አ​ብም በም​ድር ላይ በግ​ን​ባሩ ወድቆ ሰገ​ደ​ለት፤ ንጉ​ሡ​ንም አመ​ሰ​ገነ፤ ኢዮ​አ​ብም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ የአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህን ነገር አድ​ር​ገ​ሃ​ልና በዐ​ይ​ንህ ፊት ሞገ​ስን እን​ዳ​ገኘ አገ​ል​ጋ​ይህ ዛሬ ዐወቀ” አለ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ኢዮአብም አክብሮቱን ለንጉሡ ለመግለጥ ወደ መሬት በግምባሩ ተደፍቶ እጅ ነሣ፤ ንጉሡንም ባረከ፣ ኢዮአብም በመቀጠል፣ “ንጉሡ የአገልጋዩን ልመና ስለ ተቀበለው፣ ባሪያህ በፊትህ ሞገስ ማግኘቱን ዛሬ ለማወቅ ችሏል” አለ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ኢዮአብም መሬት ላይ በግምባሩ ተደፍቶ እጅ ነሣ፤ ንጉሡንም ባርኮ፥ ኢዮአብ፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ የአገልጋይህን ልመና ስለተቀበልከኝ፥ አገልጋይህ በፊትህ ሞገስ ማግኘቴን ዛሬ ለማወቅ ችያለሁ” አለ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ኢዮአብም በዳዊት ፊት ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ በመንሣት በአክብሮት ንጉሡን አመሰገነ፤ “የፈለግኹትን እንዳደርግ በመፍቀድህ በፊትህ ሞገስ ማግኘቴን አሁን ተረዳሁ” አለ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ኢዮአብም በምድር ላይ በግምባሩ ወድቆ እጅ ነሣ፥ ንጉሡንም ባረከ፥ ኢዮአብም፦ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ የባሪያህን ነገር አድርገሃልና በዓይንህ ፊት ሞገስ እንዳገኘ ባሪያህ ዛሬ አወቀ አለ።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 14:22
13 Cross References  

ድሆች አል​መ​ረ​ቁኝ እንደ ሆነ፥ በበ​ጎ​ቼም ጠጕር ትከ​ሻ​ቸው አል​ሞቀ እንደ ሆነ፥


የሰ​ማ​ች​ኝም ጆሮ ብፁዕ አለ​ችኝ፥ ያየ​ች​ኝም ዐይን ገለል አለች፤


ሕዝ​ቡም በፈ​ቃ​ዳ​ቸው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለመ​ቀ​መጥ የወ​ደ​ዱ​ትን ሰዎች ሁሉ ባረኩ።


ሕዝ​ቡም ሁሉ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገሩ፤ ንጉ​ሡም ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገረ፤ ንጉ​ሡም ቤር​ዜ​ሊን አቅፎ ሳመው፤ መረ​ቀ​ውም፤ ወደ ስፍ​ራ​ውም ተመ​ለሰ።


ዳዊ​ትም፥ “እኔ በፊ​ትህ ሞገ​ስን እን​ዳ​ገ​ኘሁ አባ​ትህ በእ​ው​ነት ያው​ቃል፤ እር​ሱም፦ ዮና​ታን እን​ዳ​ይ​ቃ​ወም አይ​ወቅ ይላል፤ ነገር ግን ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! በሕ​ያው ነፍ​ስ​ህም እም​ላ​ለሁ፤ እኔ እን​ዳ​ል​ሁት በእ​ኔና በሞት መካ​ከል አንድ ርምጃ ያህል ቀር​ቶ​አል” ብሎ ማለ።


ሞዓባዊቱም ሩት ኑኃሚንን፦ በፊቱ ሞገስ የማገኘውን ተከትዬ እህል እንድቃርም ወደ እርሻ ልሂድ አለቻት። እርስዋም፦ ልጄ ሆይ፥ ሂጂ አለቻት።


ኖኅ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሞገ​ስን አገኘ።


ዮሴ​ፍም ያዕ​ቆ​ብን አባ​ቱን አስ​ገ​ብቶ በፈ​ር​ዖን ፊት አቆ​መው፤ ያዕ​ቆ​ብም ፈር​ዖ​ንን ባረ​ከው።


ንጉ​ሡም ኢዮ​አ​ብን፥ “እነሆ፥ ይህን ነገር አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ ሂድና ብላ​ቴ​ና​ውን አቤ​ሴ​ሎ​ምን መል​ሰው” አለው።


ኢዮ​አ​ብም ተነ​ሥቶ ወደ ጌድ​ሶር ሄደ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ም​ንም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አመ​ጣው።


እን​ዲ​ሁም የቴ​ቁ​ሔ​ዪቱ ሴት ወደ ንጉሥ ገብታ በግ​ን​ባ​ርዋ በም​ድር ላይ ወደ​ቀች፤ ሰግ​ዳም “ንጉሥ ሆይ፥ አድ​ነኝ፤ አድ​ነኝ” አለች።


Follow us:

Advertisements


Advertisements