Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 14:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ንጉ​ሡም ለሴ​ቲቱ መልሶ፥ “የም​ጠ​ይ​ቅ​ሽን ነገር አት​ሰ​ው​ሪኝ” አላት። ሴቲ​ቱም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ይና​ገር” አለች።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ከዚያም ንጉሡ ሴቲቱን፣ “እኔም ለምጠይቅሽ ነገር አንቺም መልሱን አትደብቂኝ” አላት። ሴቲቱም፣ “ንጉሥ ጌታዬ፤ ዕሺ ይናገር” አለችው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ከዚያም ንጉሡ ሴቲቱን፥ “የምጠይቅሽን ነገር አንድም ሳትደብቂኝ መልሽልኝ” አላት። ሴቲቱም፥ “ንጉሥ ሆይ! ጠይቀኝ” አለችው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ንጉሡም “አንድ ጥያቄ እጠይቅሻለሁ፤ አንቺም እውነቱን በሙሉ ንገሪኝ” አላት። እርስዋም “ንጉሥ ሆይ! የፈለግኸውን ጠይቀኝ” አለችው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ንጉሡም ለሴቲቱ መልሶ፦ የምጠይቅሽን ነገር አትሰውሪኝ አላት። ሴቲቱም፦ ጌታዬ ንጉሥ ይናገር አለች።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 14:18
5 Cross References  

አለ​ቆቹ ግን እኔ ከአ​ንተ ጋር እንደ ተነ​ጋ​ገ​ርሁ ቢሰሙ፥ ወደ አን​ተም መጥ​ተው፦ ለን​ጉሡ ያል​ኸ​ውን ንገ​ረን፤ አት​ሸ​ሽ​ገ​ንም፤ እኛም አን​ገ​ድ​ል​ህም፤ ደግሞ ንጉሡ ያለ​ህን ንገ​ረን ቢሉህ፥


ንጉ​ሡም ሴዴ​ቅ​ያስ ልኮ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ነበ​ረው ወደ ሦስ​ተ​ኛው መግ​ቢያ ወደ እርሱ ነቢ​ዩን ኤር​ም​ያ​ስን አስ​መ​ጣው፤ ንጉ​ሡም ኤር​ም​ያ​ስን፥ “አን​ዲት ነገር እጠ​ይ​ቅ​ሃ​ለሁ፤ ምንም አት​ሸ​ሽ​ገኝ” አለው።


ያችም ሴት አለች፥ “መል​ካ​ሙ​ንና ክፉ​ውን ነገር ለመ​ስ​ማት ንጉሡ ጌታዬ እንደ መሥ​ዋ​ዕ​ትና እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ነውና የጌ​ታዬ የን​ጉሡ ቃል እን​ደ​ዚሁ ነው፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ይሁን።”


ንጉ​ሡም፥ “በዚህ ሁሉ ነገር የኢ​ዮ​አብ እጅ ከአ​ንቺ ጋር አለን?” አላት። ሴቲ​ቱም ንጉ​ሡን አለ​ችው፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ በሕ​ያው ነፍ​ስህ እም​ላ​ለሁ! ጌታዬ ንጉሥ ከተ​ና​ገ​ረው ነገር ሁሉ ወደ ቀኝም ወደ ግራም ሊል የሚ​ችል የለም፤ አገ​ል​ጋ​ይህ ኢዮ​አብ አዝ​ዞ​ኛል፤ ይህ​ንም ቃል ሁሉ በአ​ገ​ል​ጋ​ይህ አፍ አደ​ረ​ገው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements