Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 14:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 አሁ​ንም ሕዝቡ ስለ​ሚ​ያ​ዩኝ ይህን ነገር ለጌ​ታዬ ለን​ጉሥ እነ​ግ​ረው ዘንድ መጥ​ቻ​ለሁ፤ እኔም አገ​ል​ጋ​ይህ፦ የእ​ኔን የአ​ገ​ል​ጋ​ዩን ልመና ንጉሡ ያደ​ር​ግ​ልኝ እንደ ሆነ ለጌ​ታዬ ለን​ጉሥ ልና​ገር፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 “አሁንም ወደዚህ የመጣሁት ሕዝቡ ስላስፈራኝ ይህንኑ ለንጉሥ ጌታዬ ለመንገር ነው። እኔም አገልጋይህ ይህን አሰብሁ፤ ‘ለንጉሡ እነግረዋለሁ፤ ምናልባትም አገልጋዩ የጠየቀችውን ይፈጽምላት ይሆናል፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 አሁንም ወደዚህ የመጣሁት ሕዝቡ ስላስፈራኝ ይህንኑ ለንጉሥ ጌታዬ ለመንገር ነው። እኔም አገልጋይህ ‘ለንጉሡ እነግረዋለሁ፤ ምናልባትም አገልጋዩ የጠየቀችውን ይፈጽምላት ይሆናል፤’ ብዬ አሰብሁ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 አሁንም ንጉሥ ሆይ፥ እኔ ወደ አንተ የመጣሁት በዚህ ነገር ሰዎች ያስፈራሩኝ መሆኑን ልነግርህ ነው፤ ‘የጠየቅሁትን ሁሉ ያደርግልኛል’ በሚል ተስፋም በፊትህ ቀርቤአለሁ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 አሁንም ሕዝቡ ስለሚያስፈራኝ ይህን ነገር ለጌታዬ ለንጉሥ እነግረው ዘንድ መጥቻለሁ፥ እኔም ባሪያህ፦ ምናልባት የእኔን የባሪያውን ልመና ንጉሡ ያደርግልኝ እንደሆነ ለንጉሡ ልናገር፥

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 14:15
3 Cross References  

ሞትን እን​ሞ​ታ​ለ​ንና፥ በም​ድ​ርም ላይ እንደ ፈሰ​ሰና እን​ደ​ማ​ይ​መ​ለስ ውኃ እን​ሆ​ና​ለ​ንና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ነፍ​ስን ይወ​ስ​ዳል። የተ​ጣ​ለ​ው​ንም ከእ​ርሱ ያርቅ ዘንድ ያስ​ባል።


እኔ​ንና ልጄን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት ያር​ቀን ዘንድ ከሚሻ ሰው እጅ ያድን ዘንድ ንጉሡ አገ​ል​ጋ​ዩን ይሰ​ማል አልሁ።”


የኃ​ጥ​ኣን ሞታ​ቸው ክፉ ነውና፥ በጻ​ድ​ቃን ይስ​ቃሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements