2 ሳሙኤል 13:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 ከሁለት ዓመትም በኋላ አቤሴሎም በኤፍሬም አቅራቢያ ባለችው በቤላሶር በጎቹን በሚያሸልትበት ጊዜ አቤሴሎም የንጉሡን ልጆች ሁሉ ጠራ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም23 ከሁለት ዓመት በኋላ አቤሴሎም በኤፍሬም ድንበር አቅራቢያ ባለችው በቤላሶር ከተማ በጎቹን ይሸልት ነበር፤ በዚህ ጊዜ የንጉሡን ወንዶች ልጆች ሁሉ በዚያ እንዲገኙለት ጋበዛቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 ከሁለት ዓመት በኋላ አቤሴሎም በኤፍሬም አቅራቢያ ባለችው በበዓለ ሐጾር ከተማ በጎቹን ይሸልት ነበር፤ ከዚያም የንጉሡን ወንዶች ልጆች ሁሉ በዚያ እንዲገኙለት አቤሴሎም ጋበዛቸው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 ከሁለት ዓመት በኋላ አቤሴሎም በኤፍሬም ከተማ አጠገብ በዓለ ሐጾር ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በጎቹን ይሸልት ነበር፤ ስለዚህም የንጉሡን ወንዶች ልጆች ሁሉ ለግብዣ ወደዚያ ጠራ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 ከሁለት ዓመትም በኋላ አቤሴሎም በኤፍሬም አቅራቢያ ባለችው በቤላሶር በጎቹን አሸለተ፥ አቤሴሎምም የንጉሡን ልጆች ሁሉ ጠራ። See the chapter |