2 ሳሙኤል 12:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 ለድሃው ግን ከገዛት አንዲት ታናሽ በግ በቀር አንዳች አልነበረውም፤ አሳደጋትም፤ ተንከባከባትም፤ ከእርሱና ከልጆቹ ጋር አደገች፤ ከእንጀራውም ትበላ፥ ከዋንጫውም ትጠጣ፥ በብብቱም ትተኛ ነበረ፤ እንደ ልጁም ነበረች። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 ድኻው ግን ከገዛት ከአንዲት ጠቦት በግ በቀር ሌላ አልነበረውም። ተንከባከባት፤ ዐብራውም ከልጆቹ ጋራ አደገች፤ ዐብራው ትበላ፤ ከጽዋው ትጠጣ እንዲሁም በዕቅፉ ትተኛ ነበር፤ ልክ እንደ ገዛ ልጁ ነበረች። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ድኻው ግን ከገዛት ከአንዲት ጠቦት በግ በስተቀር ሌላ አልነበረውም። እየተንከባከበ አብራውም ከልጆቹ ጋር አደገች፤ አብራው ትበላ፤ ከጽዋውም ትጠጣ እንዲሁም በዕቅፉ ትተኛ ነበር፤ ልክ እንደገዛ ልጁ ነበረች። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 ድኻው ግን በገንዘቡ የገዛት አንዲት የበግ ግልገል ብቻ ነበረችው፤ እርስዋን እየተንከባከበ ከልጆቹ ጋር በቤቱ ውስጥ ያሳድጋት ነበር፤ ከሚመገበው ይመግባት፥ ከሚጠጣውም ያጠጣት ነበር፤ ስትተኛም ያቅፋት ነበር፤ ያቺም ግልገል ልክ እንደ ልጁ ነበረች፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 ለድሀው ግን ከገዛት አንዲት ታናሽ በግ በቀር አንዳች አልነበረውም፥ አሳደጋትም፥ ከልጆቹም ጋር በእርሱ ዘንድ አደገች፥ እንጀራውንም ትበላ፥ ከዋንጫውም ትጠጣ፥ በብብቱም ትተኛ ነበር፥ እንደ ልጁም ነበረች። See the chapter |