Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 12:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ደግ​ሞም በነ​ቢዩ በና​ታን እጅ ልኮ ስሙን ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍቁረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብሎ ጠራው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 እግዚአብሔር ሕፃኑን ስለ ወደደውም ስሙ ይዲድያ ተብሎ እንዲጠራ በነቢዩ በናታን በኩል ቃል ላከ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ጌታ ሕፃኑን ስለ ወደደም ስሙ ይዲድያ ተብሎ እንዲጠራ በነቢዩ በናታን በኩል ቃል ላከ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 “ይዲድያ” የሚል ስም እንዲያወጣለት ነቢዩ ናታንን አዘዘው፤ ይህም “በእግዚአብሔር የተወደደ” ማለት ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ደግሞም በነቢዩ በናታን እጅ ልኮ ስሙን ስለ እግዚአብሔር ይዲድያ ብሎ ጠራው።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 12:25
14 Cross References  

የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ሰሎ​ሞን በዚህ ነገር ኀጢ​አት አድ​ርጎ የለ​ምን? በብዙ አሕ​ዛ​ብም መካ​ከል እንደ እርሱ ያለ ንጉሥ አል​ነ​በ​ረም፤ በአ​ም​ላ​ኩም ዘንድ የተ​ወ​ደደ ነበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ላይ አን​ግ​ሦት ነበር፤ እር​ሱ​ንም እንኳ እን​ግ​ዶች ሴቶች አሳ​ቱት።


በዚ​ያም ሌሊት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ናታን መጣ፤ እን​ዲ​ህም አለው፦


ናታ​ንም የሰ​ሎ​ሞ​ንን እናት ቤር​ሳ​ቤ​ህን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራት፥ “ጌታ​ችን ዳዊት ሳያ​ውቅ የአ​ጊት ልጅ አዶ​ን​ያስ እንደ ነገሠ አል​ሰ​ማ​ሽ​ምን?


እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ እነሆም፥ ከደመናው “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት፤” የሚል ድምፅ መጣ።


እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው” አለ።


ለን​ጉ​ሡም፥ “እነሆ፥ ነቢዩ ናታን መጥ​ቶ​አል” ብለው ነገ​ሩት፤ እር​ሱም ወደ ንጉሡ ፊት በገባ ጊዜ በግ​ን​ባሩ በም​ድር ላይ ተደ​ፍቶ ለን​ጉሡ እጅ ነሣ።


ዳዊ​ትም ሚስ​ቱን ቤር​ሳ​ቤ​ህን አጽ​ና​ናት፤ ወደ እር​ስ​ዋም ገባ፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር ተኛ፤ ፀነ​ሰ​ችም፤ ወንድ ልጅም ወለ​ደች፤ ስሙ​ንም ሰሎ​ሞን ብሎ ጠራው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ​ደው።


ኢዮ​አ​ብም የአ​ሞ​ንን ልጆች ከተማ ራባ​ትን ወጋ፤ የመ​ን​ግ​ሥ​ታ​ቸ​ው​ንም ከተማ ያዘ።


እነ​ዚህ ደግሞ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ ከዓ​ሚል ልጅ ከቤ​ር​ሳ​ቤህ ስማዕ፥ ሶባብ፥ ናታን፥ ሰሎ​ሞን፥ አራት፤


እነሆ፥ ልጅ ይወ​ለ​ድ​ል​ሃል፤ የዕ​ረ​ፍት ሰውም ይሆ​ናል፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ካሉ ከጠ​ላ​ቶቹ ሁሉ አሳ​ር​ፈ​ዋ​ለሁ፤ ስሙ ሰሎ​ሞን ይባ​ላ​ልና፥ በዘ​መ​ኑም ሰላ​ም​ንና ጸጥ​ታን ለእ​ስ​ራ​ኤል እሰ​ጣ​ለሁ።


ስለ ብን​ያ​ምም እን​ዲህ አለ፦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ወ​ደደ በእ​ርሱ ዘንድ ተማ​ምኖ ይኖ​ራል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዘ​መኑ ሁሉ ይጋ​ር​ደ​ዋል፤ በት​ከ​ሻ​ውም መካ​ከል ያድ​ራል።


ነገር ግን ካህኑ ሳዶ​ቅና የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያስ ነቢ​ዩም ናታን፥ ሳሚም፥ ሬሲም፥ የዳ​ዊ​ትም ኀያ​ላን አዶ​ን​ያ​ስን አል​ተ​ከ​ተ​ሉም ነበር።


የና​ታ​ንም ልጅ ኦርኒያ የሹ​ሞች አለቃ ነበረ፤ የና​ታ​ንም ልጅ ዘባት የን​ጉሡ አማ​ካ​ሪና ወዳጅ ነበረ፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements