2 ሳሙኤል 12:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 ብላቴኖቹም፥ “ይህ ስለ ሕፃኑ ያደረግኸው ነገር ምንድን ነው? እርሱ በሕይወት ሳለ ጾምህና አለቀስህ፤ እንቅልፍም አጣህ፤ ሕፃኑ ከሞተ በኋላ ግን ተነሥተህ እንጀራ በላህ፤ ጠጣህም” አሉት። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም21 አገልጋዮቹም፣ “እንደዚህ ያደረግኸው ለምንድን ነው? ሕፃኑ በሕይወት እያለ ጾምህ፤ አለቀስህ፤ ሕፃኑ ከሞተ በኋላ ግን ተነሥተህ በላህ” ብለው ጠየቁት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 አገልጋዮቹም፥ “እንደዚህ ያደረግኸው ለምንድን ነው? ሕፃኑ በሕይወት እያለ ጾምህ፤ አለቀስህ፤ ሕፃኑ ከሞተ በኋላ ግን ተነሥተህ በላህ” ብለው ጠየቁት። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 ባለሟሎቹም “ይህ ነገር ምን እንደ ሆነ ለማወቅ አልቻልንም፤ ሕፃኑ በሕይወት በነበረበት ጊዜ በመጾም አለቀስክለት፤ እርሱ ከሞተ በኋላ ግን ወዲያውኑ ተነሥተህ ተመገብክ!” አሉት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 በፊቱም አቀረቡለት፥ በላም። ባሪያዎቹም፦ ይህ ያደረግኸው ነገር ምንድር ነው? በሕይወት ሳለ ስለ ሕፃኑ ጾምህና አለቀስህ፥ ከሞተ በኋላ ግን ተነሥተህ እንጀራ በላህ አሉት። See the chapter |