Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 11:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ውም ዳዊ​ትን፥ “ሰዎቹ በረ​ቱ​ብን፤ ወደ ሜዳም ወጡ​ብን፤ እኛም እስከ በሩ መግ​ቢያ ድረስ አሳ​ደ​ድ​ና​ቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 መልእክተኛውም ለዳዊት እንዲህ አለው፤ “ሰዎቹ ዐየሉብን፤ እኛንም ለመውጋት ወጥተው እስከ ሜዳው ድረስ መጡ፤ እኛ ግን እስከ ከተማዪቱ ቅጽር መግቢያ ድረስ አሳድደን መለስናቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 መልእክተኛውም ለዳዊት እንዲህ አለው፤ “ሰዎቹ አየሉብን፤ እኛንም ለመውጋት ወጥተው እስከ ሜዳው ድረስ መጡ፤ እኛ ግን እስከ ከተማዪቱ ቅጽር መግቢያ ድረስ አሳደን መለስናቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 “ጠላቶቻችን ስለ በረቱብን እኛን ለመውጋት ከከተማይቱ ወጥተው ወደ ሜዳ መጡ፤ እኛ ግን አሳደን ወደ ከተማይቱ ቅጽር በር መለስናቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 መልእክተኛውም ዳዊትን፦ ሰዎቹ በረቱብን፥ ወደ ሜዳም ወጡብን፥ እኛም ወደቅንባቸው፥ እስከ ከተማይቱም በር ድረስ ተከተልናቸው።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 11:23
2 Cross References  

የኢ​ዮ​አ​ብም መል​እ​ክ​ተኛ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ንጉሡ ሄደ። ደር​ሶም ኢዮ​አብ የነ​ገ​ረ​ውን የጦ​ር​ነ​ቱን ዜና ሁሉ ለዳ​ዊት ነገ​ረው። ዳዊ​ትም በኢ​ዮ​አብ ላይ ተቈጣ። ያንም መል​እ​ክ​ተኛ፥ “ትዋጉ ዘንድ ወደ ከተ​ማዋ ቅጥር ለምን ቀረ​ባ​ችሁ? በቅ​ጥ​ሩም እን​ደ​ም​ት​ቈ​ስሉ አታ​ው​ቁ​ምን? የይ​ሩ​በ​ዓል ልጅ አቤ​ሜ​ሌ​ክን ማን ገደ​ለው? አን​ዲት ሴት ከቅ​ጥር ላይ የወ​ፍጮ መጅ ጥላ​በት በቴ​ቤስ የሞተ አይ​ደ​ለ​ምን? ስለ​ምን ወደ ቅጥሩ ቀረ​ባ​ችሁ?” አለው።


ፍላ​ጻም የሚ​ወ​ረ​ውሩ በቅ​ጥሩ ላይ ሆነው በአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ላይ ወረ​ወሩ፤ ከን​ጉ​ሡም ብላ​ቴ​ኖች አን​ዳ​ንድ ሞቱ፤ አገ​ል​ጋ​ይህ ኬጤ​ያ​ዊው ኦርዮ ደግሞ ሞተ” አለው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements