Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 11:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የኔር ልጅ የይ​ሩ​በ​ዓ​ልን ልጅ አቤ​ሜ​ሌ​ክን ማን ገደ​ለው? አን​ዲት ሴት ከቅ​ጥር ላይ የወ​ፍጮ መጅ ጥላ​በት የሞተ አይ​ደ​ለ​ምን? ስለ​ምን ወደ ቅጥሩ እን​ደ​ዚህ ቀረ​ባ​ችሁ? አን​ተም፦ ባሪ​ያህ ኬጤ​ያ​ዊው ኦርዮ ደግሞ ሞተ በለው።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 የይሩቤሼትን ልጅ አቢሜሌክን የገደለው ማነው? በቴቤስ ከግንብ ቅጥር የወፍጮ መጅ ለቅቃበት የገደለችው አንዲት ሴት አይደለችምን? ታዲያ እናንተስ ወደ ግንቡ ቅጥር ይህን ያህል የተጠጋችሁት ለምንድን ነው?’ በማለት ቢጠይቅህ፣ አንተም መልሰህ፣ ‘አገልጋይህ ኬጢያዊው ኦርዮም ሞቷል’ ብለህ ንገረው።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 የይሩቤሼትን ልጅ አቤሜሌክን የገደለው ማነው? በቴቤጽ ከግንብ ቅጥር የወፍጮ መጅ ለቃበት የገደለችው አንዲት ሴት አይደለችምን? ታዲያ እናንተስ ወደ ግንቡ ቅጥር ይህን ያህል የተጠጋችሁት ለምንድን ነው?’ አንተም መልሰህ፥ ‘አገልጋይህ ሒታዊው ኦርዮም ሞቷል’ ብለህ ንገረው።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 የጌዴዎን ልጅ አቤሜሌክ እንዴት እንደ ሞተ አታስታውሱምን? እርሱን ቴቤጽ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ አንዲት ሴት ከግንብ ላይ የወፍጮ ድንጋይ ናዳ በመጣል ገደለችው፤ ታዲያ እናንተ ወደ ግንብ የተጠጋችሁት ለምንድን ነው?’ ንጉሡ ይህን ጥያቄ ቢያቀርብልህ፥ ‘የጦር መኰንንህ ኦርዮም ተገድሎአል’ ብለህ ንገረው።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 የሩቤሼትን ልጅ አቤሜሌክን ማን ገደለው? ከቅጥር ላይ የወፍጮ መጅ ጥላ በቴቤስ ላይ የገደለችው አንዲት ሴት አይደለችምን? ስለ ምን ወደ ቅጥሩ እንደዚህ ቀርባችሁ? ብሎ ንጉሡ ሲቆጣ ብታይ፥ አንተ፦ ባሪያህ ኬጢያዊው ኦርዮ ደግሞ ሞተ በለው።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 11:21
11 Cross References  

ጌዴ​ዎን የተ​ባ​ለ​ውም ይሩ​በ​ኣል ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ሕዝብ ሁሉ ማል​ደው ተነሡ፤ በአ​ሮ​ኤድ ምንጭ አጠ​ገብ ሰፈሩ፤ የም​ድ​ያ​ምም ሰፈር ከእ​ነ​ርሱ ወደ ሰሜን በኩል በሞሬ ኮረ​ብታ አጠ​ገብ በሸ​ለ​ቆው ውስጥ ነበረ።


እጆ​ችህ አል​ታ​ሰ​ሩም፤ እግ​ሮ​ች​ህም በሰ​ን​ሰ​ለት አል​ተ​ያ​ዙም፤ ማንም እንደ ሰነፍ አል​ወ​ሰ​ደ​ህም፤ በዐ​መፃ ልጆ​ችም ፊት ወደ​ቅህ።” ሕዝ​ቡም ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው አለ​ቀ​ሱ​ለት።


አበ​ኔ​ርም ወደ ኬብ​ሮን በተ​መ​ለሰ ጊዜ ኢዮ​አብ በበር ውስጥ በቈ​ይታ ይና​ገ​ረው ዘንድ ወደ አጠ​ገቡ ወሰ​ደው፤ በዚ​ያም ለወ​ን​ድሙ ለአ​ሣ​ሄል ደም ተበ​ቅሎ ወገ​ቡን መታው፤ ሞተም።


በዚ​ያች ቀንም መሠ​ዊ​ያ​ዉን አፍ​ር​ሶ​አ​ልና በዓል ከእ​ርሱ ጋር ይሟ​ገት ሲል ጌዴ​ዎ​ንን ይሩ​በ​ኣል ብሎ ጠራው።


እነ​ዚህ ሁሉ፦ አንተ ደግሞ እንደ እኛ ተይ​ዘ​ሃል፤ እንደ እኛም ተቈ​ጥ​ረ​ሃል።


አም​ላኬ ሆይ፥ ፈቃ​ድ​ህን ለማ​ድ​ረግ መከ​ርሁ፥ ሕግ​ህም በልቤ ውስጥ ነው።”


የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ሰዎች ወጥ​ተው ከኢ​ዮ​አብ ጋር ተዋጉ፤ ከዳ​ዊ​ትም አገ​ል​ጋ​ዮች ከሕ​ዝቡ አን​ዳ​ንዱ ወደቁ፤ ኬጤ​ያ​ዊው ኦር​ዮም ደግሞ ሞተ።


ንጉሡ ቢቈጣ፥ እን​ዲ​ህም ቢል፦ ልትዋጉ ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ለምን ቀረ​ባ​ችሁ? ከቅ​ጥሩ በላይ ፍላጻ እን​ዲ​ወ​ረ​ወር አታ​ው​ቁ​ምን?


የኢ​ዮ​አ​ብም መል​እ​ክ​ተኛ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ንጉሡ ሄደ። ደር​ሶም ኢዮ​አብ የነ​ገ​ረ​ውን የጦ​ር​ነ​ቱን ዜና ሁሉ ለዳ​ዊት ነገ​ረው። ዳዊ​ትም በኢ​ዮ​አብ ላይ ተቈጣ። ያንም መል​እ​ክ​ተኛ፥ “ትዋጉ ዘንድ ወደ ከተ​ማዋ ቅጥር ለምን ቀረ​ባ​ችሁ? በቅ​ጥ​ሩም እን​ደ​ም​ት​ቈ​ስሉ አታ​ው​ቁ​ምን? የይ​ሩ​በ​ዓል ልጅ አቤ​ሜ​ሌ​ክን ማን ገደ​ለው? አን​ዲት ሴት ከቅ​ጥር ላይ የወ​ፍጮ መጅ ጥላ​በት በቴ​ቤስ የሞተ አይ​ደ​ለ​ምን? ስለ​ምን ወደ ቅጥሩ ቀረ​ባ​ችሁ?” አለው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements