Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 11:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ኢዮ​አ​ብም ከተ​ማ​ዪ​ቱን በከ​በበ ጊዜ ጀግ​ኖች እን​ዳ​ሉ​በት በሚ​ያ​ው​ቀው ስፍራ ኦር​ዮን አቆ​መው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ስለዚህም ኢዮአብ ከተማዪቱን በከበባት ጊዜ፣ እጅግ ጠንካራ ተከላካዮች እንዳሉበት በሚያውቀው ግንባር ኦርዮን መደበው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ስለዚህም ኢዮአብ ከተማዪቱን በከበባት ጊዜ፥ እጅግ ጠንካራ ተከላካዮች እንዳሉበት በሚያውቀው ግንባር ኦርዮንን መደበው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 በዚህ ዐይነት ኢዮአብ ከተማይቱን ከቦ በመያዝ ላይ ሳለ ጠላት ማየሉን በሚያውቅበት ስፍራ ኦርዮን አሰለፈው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ኢዮአብም ከተማይቱን በከበበ ጊዜ ጀግኖች እንዳሉበት በሚያውቀው ስፍራ ኦርዮን አቆመው።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 11:16
13 Cross References  

ጴጥ​ሮ​ስና ሐዋ​ር​ያ​ትም መል​ሰው እን​ዲህ አሉ​አ​ቸው፥ “ለሰው ከመ​ታ​ዘዝ ይልቅ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መታ​ዘዝ ይገ​ባል።


ኤፍ​ሬም የተ​ገፋ ሆነ፤ በፍ​ር​ድም ተረ​ገጠ፤ ከን​ቱን ይከ​ተል ዘንድ ጀም​ሮ​አ​ልና።


ከዚ​ህም በኋላ ኢዩ፥ “ወገ​ኖ​ቼስ ከሆ​ና​ችሁ፥ ነገ​ሬ​ንም ከሰ​ማ​ችሁ የጌ​ታ​ች​ሁን ልጆች ራስ ቍረጡ፤ ነገም በዚህ ሰዓት ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ወደ እኔ ይዛ​ችሁ ኑ” ብሎ ሁለ​ተኛ ደብ​ዳቤ ጻፈ​ላ​ቸው። የን​ጉ​ሡም ልጆች ሰባው ሰዎች በሚ​ያ​ሳ​ድ​ጓ​ቸው በከ​ተ​ማ​ዪቱ ታላ​ላ​ቆች ዘንድ ነበሩ።


አን​ተም ደግሞ የሶ​ር​ህያ ልጅ ኢዮ​አብ፥ ሁለ​ቱን የእ​ስ​ራ​ኤል ሠራ​ዊት አለ​ቆች የኔር ልጅ አበ​ኔ​ርን የኢ​ያ​ቴ​ር​ንም ልጅ አሜ​ሳ​ይን ገድሎ፥ በእኔ ላይ ያደ​ረ​ገ​ውን ታው​ቃ​ለህ፤ የጦ​ር​ነ​ት​ንም ደም በሰ​ላም አፈ​ሰሰ፤ በወ​ገ​ቡም ባለው ድግና በእ​ግ​ሩም ባለው ጫማ ንጹሕ ደም አኖረ።


የኔር ልጅ የይ​ሩ​በ​ዓ​ልን ልጅ አቤ​ሜ​ሌ​ክን ማን ገደ​ለው? አን​ዲት ሴት ከቅ​ጥር ላይ የወ​ፍጮ መጅ ጥላ​በት የሞተ አይ​ደ​ለ​ምን? ስለ​ምን ወደ ቅጥሩ እን​ደ​ዚህ ቀረ​ባ​ችሁ? አን​ተም፦ ባሪ​ያህ ኬጤ​ያ​ዊው ኦርዮ ደግሞ ሞተ በለው።”


አበ​ኔ​ርም ወደ ኬብ​ሮን በተ​መ​ለሰ ጊዜ ኢዮ​አብ በበር ውስጥ በቈ​ይታ ይና​ገ​ረው ዘንድ ወደ አጠ​ገቡ ወሰ​ደው፤ በዚ​ያም ለወ​ን​ድሙ ለአ​ሣ​ሄል ደም ተበ​ቅሎ ወገ​ቡን መታው፤ ሞተም።


በደ​ብ​ዳ​ቤ​ውም፥ “ኦር​ዮን ጽኑ ሰልፍ ባለ​በት በፊ​ተ​ኛው ስፍራ አቁ​ሙት፤ ተወ​ግ​ቶም ይሞት ዘንድ ከኋላ ሽሹ” ብሎ ጻፈ።


የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ሰዎች ወጥ​ተው ከኢ​ዮ​አብ ጋር ተዋጉ፤ ከዳ​ዊ​ትም አገ​ል​ጋ​ዮች ከሕ​ዝቡ አን​ዳ​ንዱ ወደቁ፤ ኬጤ​ያ​ዊው ኦር​ዮም ደግሞ ሞተ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements