Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 11:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በደ​ብ​ዳ​ቤ​ውም፥ “ኦር​ዮን ጽኑ ሰልፍ ባለ​በት በፊ​ተ​ኛው ስፍራ አቁ​ሙት፤ ተወ​ግ​ቶም ይሞት ዘንድ ከኋላ ሽሹ” ብሎ ጻፈ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 በደብዳቤውም ላይ፣ “ኦርዮ ውጊያው በተፋፋመበት ግንባር መድበው፤ ከዚያም ተወግቶ እንዲሞት ትታችሁት ሽሹ” ብሎ ጻፈ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 በደብዳቤውም ላይ፥ “ኦርዮን ውጊያው በተፋፋመበት ግንባር መድበው፤ ከዚያም ተወግቶ እንዲሞት ትታችሁት ሽሹ” ብሎ ጻፈ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የጻፈውም ቃል “ኦርዮን ጦርነቱ በተፋፋመበት ግንባር አሰልፈው፤ ከዚያም አንተ ወደ ኋላ አፈግፍገህ እርሱ እንዲገደል አድርገው” የሚል ነበር።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በደብዳቤውም፦ ኦርዮን ጽኑ ሰልፍ ባለበት በፊተኛው ስፍራ አቁሙት፥ ተመትቶም ይሞት ዘንድ ከኋላው ሽሹ ብሎ ጻፈ።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 11:15
12 Cross References  

አሁ​ንስ በፊቱ ክፉ ትሠራ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ነገር ለምን አቃ​ለ​ልህ? ኬጤ​ያ​ዊ​ውን ኦር​ዮን በሰ​ይፍ መት​ተ​ሃል፤ ሚስ​ቱ​ንም ለአ​ንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስ​ደ​ሃል፤ እር​ሱ​ንም በአ​ሞን ልጆች ሰይፍ ገድ​ለ​ሃል።


ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን፥ “ታላ​ቂቱ ልጄ ሜሮብ እነ​ኋት፤ እር​ስ​ዋን እድ​ር​ል​ሃ​ለሁ፤ ብቻ ጀግና ልጅ ሁን​ልኝ፤ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጦር​ነት ተጋ​ደል” አለው። ሳኦ​ልም፥ “የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ በእ​ርሱ ላይ ትሁን እንጂ የእኔ እጅ በእ​ርሱ ላይ አት​ሁን” ይል ነበር።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘምሩ፤ አመ​ስ​ግ​ኑ​ትም፤ የች​ግ​ረ​ኛ​ውን ነፍስ ከክፉ አድ​ራ​ጊ​ዎች እጅ አድ​ኖ​አ​ልና።


የሚ​ያ​ሰ​ጥም የም​ላስ ነገ​ርን ሁሉ ወደ​ድህ።


የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ሰዎች ወጥ​ተው ከኢ​ዮ​አብ ጋር ተዋጉ፤ ከዳ​ዊ​ትም አገ​ል​ጋ​ዮች ከሕ​ዝቡ አን​ዳ​ንዱ ወደቁ፤ ኬጤ​ያ​ዊው ኦር​ዮም ደግሞ ሞተ።


ሳኦ​ልም አላ​ቸው፥ “የን​ጉ​ሥን ጠላ​ቶች ይበ​ቀል ዘንድ ከመቶ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሸለ​ፈት በቀር ንጉሥ ማጫ አይ​ሻም ብላ​ችሁ ለዳ​ዊት ንገ​ሩት” አላ​ቸው። ሳኦል ግን ይህን ማለቱ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ይጥ​ለው ዘንድ አስቦ ነው።


ሳኦ​ልም፥ “እር​ስ​ዋን እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋም እን​ቅ​ፋት ትሆ​ን​በ​ታ​ለች” አለ። እነ​ሆም፥ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ በሳ​ኦል ላይ ነበ​ረች።


ኢዮ​አ​ብም ከተ​ማ​ዪ​ቱን በከ​በበ ጊዜ ጀግ​ኖች እን​ዳ​ሉ​በት በሚ​ያ​ው​ቀው ስፍራ ኦር​ዮን አቆ​መው።


ከኬ​ጥ​ያ​ዊው ከኦ​ርዮ ነገር በቀር ዳዊት በዘ​መኑ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገ​ርን አድ​ርጎ ነበ​ርና፥ ካዘ​ዘ​ውም ነገር ሁሉ ፈቀቅ አላ​ለም ነበ​ርና።


ክፉን ከሚ​ያ​ደ​ርጉ ወገን ፈጥኖ ክር​ክ​ርን የሚ​ያ​ደ​ርግ የለ​ምና፤ ስለ​ዚህ የሰው ልጆች ልብ በእ​ነ​ርሱ ክፉን ለመ​ሥ​ራት ጠነ​ከረ።


“የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ጥልቅ ነው፤ ማንስ ያው​ቀ​ዋል?


Follow us:

Advertisements


Advertisements