2 ሳሙኤል 1:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 ሳኦልና ዮናታን የተወደዱና ያማሩ ነበሩ፤ በሕይወታቸውና በሞታቸው አልተለያዩም፤ ከንስር ይልቅ ፈጣኖች ነበሩ፤ ከአንበሳም ይልቅ ብርቱዎች ነበሩ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም23 ሳኦልና ዮናታን በሕይወት እያሉ፣ የሚዋደዱና የሚስማሙ ነበሩ፤ ሲሞቱም አልተለያዩም፤ ከንስርም ይልቅ ፈጣኖች፣ ከአንበሳም ይልቅ ብርቱዎች ነበሩ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 ሳኦልና ዮናታን፥ የተዋደዱና የተስማሙ፤ በሕይወትም ሆነ በሞት ያልተለያዩ፤ ከንስርም ይልቅ የፈጠኑ፥ ከአንበሳም ይልቅ ብርቱዎች ነበሩ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 “ሳኦልና ዮናታን በአስደናቂ ፍቅር ኖሩ፤ በሕይወትም ሆነ በሞት ላለመለያየት ተባበሩ፤ እነርሱም ከንስር የፈጠኑ፥ ከአንበሳም የበረቱ ነበሩ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 ሳኦልና ዮናታን የተዋደዱና የተስማሙ ነበሩ፥ በሕይወታቸውና በሞታቸው አልተለያዩም፥ ከንስር ይልቅ ፈጣኖች ነበሩ፥ ከአንበሳም ይልቅ ብርቱዎች ነበሩ። See the chapter |