Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ሳሙኤል 1:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በጦር ወድ​ቀ​ዋ​ልና ለሳ​ኦ​ልና ለልጁ ለዮ​ና​ታን፥ ለይ​ሁ​ዳም ሕዝብ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ወገን እንባ እያ​ፈ​ሰሱ አለ​ቀሱ፤ እስከ ማታም ድረስ ጾሙ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ለሳኦልና ለልጁ ለዮናታን፣ ለእግዚአብሔር ሰራዊትና ለእስራኤል ቤት ዐዘኑ፤ አለቀሱ፤ እስከ ማታም ድረስ ጾሙ፤ የወደቁት በሰይፍ ነበርና።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 የወደቁት በሰይፍ ነበርና፥ ለሳኦልና ለልጁ ለዮናታን፥ ለጌታ ሠራዊትና ለእስራኤል ቤትም አዘኑ፤ አለቀሱ፤ እስከ ማታም ድረስ ጾሙ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በሰይፍ ስለ ተገደሉ ለሳኦል፥ ለልጁ ለዮናታንና ለእግዚአብሔር ሠራዊት ለመላው እስራኤል እስከ ምሽት ድረስ በመጾም በከባድ ሐዘን አለቀሱላቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በሰይፍም ወድቀዋልና ለሳኦልና ለልጁ ለዮናታን ለእግዚአብሔርም ሕዝብ ለእስራኤልም ወገን እንባ እያፈሰሱ አለቀሱ፥ እስከ ማታም ድረስ ጾሙ።

See the chapter Copy




2 ሳሙኤል 1:12
10 Cross References  

እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፤ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፤ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፤ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።


ጠላትህ ቢወድቅ ደስ አይበልህ፥ በመሰናከሉም አትታበይ።


በመጨረሻው ሁላችሁ በአንድ ልብ ሁኑ፤ የሌላው መከራ ለእናንተ እንደሚሆን አድርጉ፤ እንደወንድሞች ተዋደዱ፤ ርኅሩኆችና ትሑታን ሁኑ፤


ታሞ እኔ የማ​ላ​ዝ​ን​ለት ማን ነው? በድ​ሎስ እኔ የማ​ል​ደ​ነ​ግ​ጥ​ለት ማን ነው?


በጽዋ የቀላ ወይን ለሚ​ጠጡ፥ እጅግ በአ​ማረ ሽቱም ለሚ​ቀቡ፥ በዮ​ሴፍ ስብ​ራት ለማ​ያ​ስቡ ወዮ​ላ​ቸው።


ሕዝ​ቡም ሁሉ ገና ሳይ​መሽ ዳዊ​ትን እን​ጀራ ይበላ ዘንድ ሊጋ​ብ​ዙት መጡ፤ ዳዊት ግን፥ “ፀሐይ ሳት​ጠ​ልቅ እን​ጀራ ወይም ሌላ ነገር ብቀ​ምስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ያድ​ር​ግ​ብኝ፥ ይህ​ንም ይጨ​ም​ር​ብኝ” ብሎ ማለ።


ስለ ተገ​ደሉ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊ​ትና ቀን አለ​ቅስ ዘንድ ለራሴ ውኃን፥ ለዐ​ይ​ኔም የዕ​ን​ባን ምንጭ ማን በሰ​ጠኝ?


አጥ​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ወሰዱ፤ በኢ​ያ​ቢ​ስም ባለው የእ​ርሻ ቦታ ቀበ​ሩ​አ​ቸው፤ ሰባት ቀንም ጾሙ።


በዚ​ያም ቀን ሳኦል ሦስ​ቱም ልጆቹ ጋሻ ጃግ​ሬ​ውም በአ​ንድ ላይ ሞቱ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements