Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 9:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 በገ​ባም ጊዜ፥ እነሆ፥ የሠ​ራ​ዊት አለ​ቆች ተቀ​ም​ጠው አገኘ፤ እር​ሱም፥ “አለቃ ሆይ፥ የም​ና​ገ​ረው መል​እ​ክት አለኝ” አለ። ኢዩም፥ “ከማ​ን​ኛ​ችን ጋር ነው?” አለ። እር​ሱም፥ “አለቃ ሆይ፥ ከአ​ንተ ጋር ነው” አለ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 በዚያ እንደ ደረሰም፣ የሰራዊቱ ጦር መኰንኖች በአንድነት ተቀምጠው ነበር፤ እርሱም “መኰንን ሆይ፤ ወደ አንተ ተልኬአለሁ” አለ። ኢዩም፣ “ለማንኛችን ነው?” ሲል ጠየቀ። እርሱም፣ “መኰንን ሆይ፤ ለአንተ ነው” ብሎ መለሰ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እዚያም እንደ ደረሰ የጦር መኰንኖች ተቀምጠው ሲወያዩ አግኝቶ “ጌታዬ ለአንተ የምሰጥህ መልእክት አለኝ” አለው። ኢዩም “ከእኛ መካከል ለማንኛችን ነው የምትናገረው?” ሲል ጠየቀው። ነቢዩም “የምናገረው ለአንተው ነው” ሲል መለሰ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እዚያም እንደ ደረሰ የጦር መኰንኖች ተቀምጠው ሲወያዩ አግኝቶ “ጌታዬ ለአንተ የምሰጥህ መልእክት አለኝ” አለው። ኢዩም “ከእኛ መካከል ለማንኛችን ነው የምትናገረው?” ሲል ጠየቀው። ነቢዩም “የምናገረው ለአንተው ነው” ሲል መለሰ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 በገባም ጊዜ፥ እነሆ፥ የሠራዊት አለቆች ተቀምጠው ነበር፤ እርሱም “አለቃ ሆይ! ለአንተ መልእክት አለኝ፤” አለ። ኢዩም “ለማንኛችን ነው?” አለ። እርሱም “አለቃ ሆይ! ለአንተ ነው፤” አለ።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 9:5
4 Cross References  

ዔግ​ሎ​ምም ከገ​ል​ገል ከጣ​ዖ​ታቱ ቤት ተመ​ለሰ። ናዖ​ድም፥ “ንጉሥ ሆይ፥ ለብ​ቻህ የም​ነ​ግ​ርህ የም​ሥ​ጢር ነገር አለኝ” አለ፤ ዔግ​ሎ​ምም ሁሉ ከእ​ርሱ ዘንድ እን​ዲ​ወጣ አዘዘ፤ በእ​ር​ሱም ዘንድ የቆ​ሙት ሁሉ ወጡ ።


በዚ​ያም በደ​ረ​ስህ ጊዜ የና​ሜ​ሲን ልጅ የኢ​ዮ​ሣ​ፍ​ጥን ልጅ ኢዩን ታገ​ኘ​ዋ​ለህ፤ ገብ​ተ​ህም ከወ​ን​ድ​ሞቹ መካ​ከል አስ​ነ​ሣው፤ ወደ ጓዳም አግ​ባው።


እን​ዲ​ሁም ጐል​ማ​ሳው ነቢይ ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ሄደ።


ተነ​ሥ​ቶም ወደ ቤቱ ገባ፥ ዘይ​ቱ​ንም በራሱ ላይ አፍ​ስሶ እን​ዲህ አለው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባ​ሁህ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements