Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 9:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ፊቱ​ንም አቅ​ንቶ በመ​ስ​ኮቱ አያት። “አንቺ ማን ነሽ? ወደ​ዚህ ወደ እኔ ውረጂ” አላት። ከዚ​ህም በኋላ ሁለት ጃን​ደ​ረ​ቦች ወደ እርሱ ተመ​ለ​ከቱ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ቀና ብሎ ወደ መስኮቱ ተመለከተና፣ “ማነህ አንተ? ማነው የሚተባበረኝ” ሲል ጮኾ ተጣራ። ሁለት ሦስት ጃንደረቦችም ቍልቍል ወደ እርሱ ተመለከቱ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ኢዩ ቀና ብሎ ወደ ላይ በመመልከት ድምፁን ከፍ አድርጎ “ከእኔ ጋር የሚተባበር ማን ነው?” ሲል ጮኸ፤ ቁጥራቸው ከሁለት እስከ ሦስት የሆነ የቤተ መንግሥት ባለ ሥልጣኖች በመስኮት ብቅ ብለው ወደ እርሱ ተመለከቱ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ኢዩ ቀና ብሎ ወደ ላይ በመመልከት ድምፁን ከፍ አድርጎ “ከእኔ ጋር የሚተባበር ማን ነው?” ሲል ጮኸ፤ ቊጥራቸው ከሁለት እስከ ሦስት የሆነ የቤተ መንግሥት ባለ ሥልጣኖች በመስኮት ብቅ ብለው ወደ እርሱ ተመለከቱ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ፊቱንም ወደ መስኮቱ አንሥቶ “ከእኔ ጋር ማን ነው?” አለ። ሁለት ሦስትም ጃንደረቦች ወደ እርሱ ተመለከቱ።

See the chapter Copy




2 ነገሥት 9:32
13 Cross References  

ሄሮ​ድ​ስም በጢ​ሮ​ስና በሲ​ዶና ሰዎች ተቈ​ጥቶ ነበር፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ወደ እርሱ መጥ​ተው የን​ጉ​ሡን ቢት​ወ​ደድ በላ​ስ​ጦ​ስን እን​ዲ​ያ​ስ​ታ​ር​ቃ​ቸው ማለ​ዱት፤ የሀ​ገ​ራ​ቸው ምግብ ከን​ጉሥ ሄር​ድስ ነበ​ርና።


ትእ​ዛ​ዝ​ህን ሁሉ ስመ​ለ​ከት በዚ​ያን ጊዜ አላ​ፍ​ርም።


በከ​ተ​ሞቹ ሁሉ አላ​ባሽ አግሬ ጋሻና ጦርን አኖረ፤ ከተ​ሞ​ቹ​ንም እጅግ አጠ​ነ​ከ​ራ​ቸው፤ ይሁ​ዳና ብን​ያ​ምም የእ​ርሱ ወገን ነበሩ።


መን​ፈ​ስም በሠ​ላ​ሳው አለቃ በዓ​ማ​ሣይ ላይ መጣ፤ እር​ሱም፥ “ዳዊት ሆይ፥ እኛ ያንተ ነን፤ የእ​ሴይ ልጅ ሆይ፥ እኛ ከአ​ንተ ጋር ነን፤ ውጣ አም​ላ​ክህ ይረ​ዳ​ሃ​ልና ሰላም ሰላም ለአ​ንተ ይሁን፤ ለሚ​ረ​ዱ​ህም ሰላም ይሁን” አለ። ዳዊ​ትም ተቀ​በ​ላ​ቸው፤ የጭ​ፍ​ራም አለ​ቆች አደ​ረ​ጋ​ቸው።


ሙሴ በሰ​ፈሩ ደጅ ቆሞ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወገን የሆነ ወደ እኔ ይምጣ” አለ፤ የሌዊ ልጆች ሁሉ ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ።


የባ​ሪ​ያ​ዎቼን የነ​ቢ​ያ​ትን ደም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ባሪ​ያ​ዎች ሁሉ ደም ከኤ​ል​ዛ​ቤል እጅና ከአ​ክ​ዓብ ቤት ሁሉ እጅ እበ​ቀል ዘንድ የጌ​ታ​ህን የአ​ክ​ዓ​ብን ቤት ታጠ​ፋ​ለህ።


ኢዩም ወደ ከተማ በገባ ጊዜ፥ “ጌታ​ውን የገ​ደለ ዘምሪ ሰላም ነውን?” አለ​ችው።


እር​ሱም፥ “ወደ ታች ወር​ው​ሩ​አት” አላ​ቸው፤ ወረ​ወ​ሩ​አ​ትም፥ ደም​ዋም በግ​ን​ቡና በፈ​ረ​ሶች መግ​ሪያ ላይ ተረጨ፥ ረገ​ጡ​አ​ትም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements