Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




2 ነገሥት 9:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ኢዩም ጋሻ​ጃ​ግ​ሬ​ውን ቢድ​ቃ​ርን እን​ዲህ አለው፥ “አን​ሥ​ተህ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊው በና​ቡቴ እርሻ ጣለው፤ አን​ተና እኔ ጎን ለጎን በፈ​ረስ ተቀ​ም​ጠን አባ​ቱን አክ​ዓ​ብን በተ​ከ​ተ​ልን ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ይህን መከራ እንደ ተና​ገ​ረ​በት እኔ አስ​ባ​ለ​ሁና አን​ተም ታው​ቃ​ለ​ህና፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ኢዩም የሠረገላ ኀላፊውን ቢድቃርን እንዲህ አለው፤ “አንሣውና በኢይዝራኤላዊው በናቡቴ ዕርሻ ላይ ጣለው፤ አንተና እኔ አባቱን አክዓብን በየሠረገሎቻችን ሆነን ተከትለነው ስንሄድ፣ እግዚአብሔር ይህን ትንቢት እንዲህ ሲል እንደ ተናገረበት አስታውስ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ኢዩ ቢድቃር ተብሎ የሚጠራውን የቅርብ ረዳቱን “ሬሳውን አንሥተህ የናቡቴ ርስት በነበረው እርሻ ላይ ወርውረህ ጣለው፤ እኔና አንተ የንጉሥ ኢዮራም አባት ከነበረው ከአክዓብ በስተ ኋላ እየጋለብን ስንሄድ እግዚአብሔር በአክዓብ ላይ የተናገረውን ቃል አስታውስ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ኢዩ ቢድቃር ተብሎ የሚጠራውን የቅርብ ረዳቱን “ሬሳውን አንሥተህ የናቡቴ ርስት በነበረው እርሻ ላይ ወርውረህ ጣለው፤ እኔና አንተ የንጉሥ ኢዮራም አባት ከነበረው ከአክዓብ በስተኋላ እየጋለብን ስንሄድ እግዚአብሔር በአክዓብ ላይ የተናገረውን ቃል አስታውስ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ኢዩም አለቃውን ቢድቃርን እንዲህ አለው “አንሥተህ በኢይዝራኤላዊው በናቡቴ እርሻ ጣለው፤ አንተና እኔ ጎን ለጎን በፈረስ ተቀምጠን አባቱን አክዓብን በተከተልን ጊዜ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ይህን መከራ እንደ ተናገረበት አስብ፤

See the chapter Copy




2 ነገሥት 9:25
12 Cross References  

እነ​ዚ​ህም የአ​ው​ራ​ጃ​ዎች አለ​ቆች ጐል​ማ​ሶች ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ወጡ፤ ሠራ​ዊ​ትም ተከ​ተ​ላ​ቸው።


የአ​ሞጽ ልጅ ኢሳ​ይ​ያስ በባ​ቢ​ሎን ላይ ያየው ራእይ።


ቀንበሬ ልዝብ፤ ሸክሜም ቀሊል ነውና።”


በሚልክያስ እጅ ለእስራኤል የሆነ የእግዚአብሔር ቃል ሸክም ይህ ነው።


ስለ ነነዌ የተነገረ ሸክም፣ የኤልቆሻዊው የናሆም የራእዩ መጽሐፍ ይህ ነው።


ከአ​ዛ​ሄ​ልም ሰይፍ የሚ​ያ​መ​ል​ጠ​ውን ሁሉ ኢዩ ይገ​ድ​ለ​ዋል፤ ከኢ​ዩም ሰይፍ የሚ​ያ​መ​ል​ጠ​ውን ሁሉ ኤል​ሳዕ ይገ​ድ​ለ​ዋል።


የሶ​ር​ያም ንጉሥ ወልደ አዴር ሠራ​ዊ​ቱን ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ ወጥ​ቶም ሰማ​ር​ያን ከበ​ባት፤ እየ​ጠ​በ​ቃ​ቸ​ውም ተቀ​መጠ። ከእ​ር​ሱም ጋር ሠላሳ ሁለት ነገ​ሥ​ታት ነበሩ፤ ፈረ​ሶ​ችና ሰረ​ገ​ሎ​ችም ነበሩ፤ ወጥ​ተ​ውም ሰማ​ር​ያን ከበ​ቧት፥ ወጓ​ትም።


በእ​ው​ነት የና​ቡ​ቴ​ንና የል​ጆ​ቹን ደም ትና​ን​ትና አይ​ቻ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ በዚ​ህም እርሻ እበ​ቀ​ለ​ዋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገ​ረው ቃል ወስ​ደህ በእ​ር​ሻው ውስጥ ጣለው።”


አን​ተም፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ይህ ሸክም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሚ​ኖ​ረው አለቃ ላይ፥ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም በሚ​ኖ​ሩት በእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ላይ ነው በላ​ቸው።


ለኢዩ፥ “ልጆ​ችህ እስከ አራት ትው​ልድ ድረስ በእ​ስ​ራ​ኤል ዙፋን ላይ ይቀ​መ​ጣሉ” ተብሎ የተ​ነ​ገ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይህ ነበረ፤ እን​ዲ​ሁም ሆነ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements